በኢሕአዴግ ተቋም ውስጥ ያለውን ውንብድና ከራሱ ከኢህአዴግ አንደበት ሲጋለጥ

(ከስር ያለው ማመልከቻ አንዲት “ከፍተኛ” አመራር ለዶ/ር አብይ የተፃፈችው ነው። ከእነ ኢህአዴግነቱ ታግሳችሁ ብታነቡት ጥሩ ትዝብት ታገኛላችሁ። እስር ቤት ውስጥ ሆኖ የደረጃ እድገት ያገኘ አለ። ተቋም ውስጥ ያለውን ውንብድና ከራሱ ከኢህአዴግ አንደበት ስሙትማ)

ሚያዚያ 19/2010

ለ፡ ክቡር የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ አብይ አህመድ

ከ፡ ወ/ሮ ሙላቷ ወልዴ

አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡ የተፈጸመብኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰትንና ህገ-መንግስቱ ያረጋግጠልኝንበህግ ፊት እኩል የመዳኘት፤ ፍትህ
የማግኘት፤ የመልካም ስም ሰብዓዊ መብቴን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ማስመለስንይመለከታል፡፡

እኔ ወ/ሮ ሙላቷ ወልዴ ከግንቦት 2002 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የፈረደራል ተቋማት በመካከለኛ አመራርነት በተለይም በመልካም አስተዳደርና በለውጥ ስራዎች ላይ ሳገለግል ቆይቻለሁ፡፡ በድርጅት መዋቅር ደግሞ በሰራሁባቸው የተለያዩ የፌደራል ተቋማት የወረዳ የኢህአዴግ ኮሚቴ አመራር በመሆን ሳገለግል የቆየሁ ሲሆን ላለፉት 9አመታትም በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የየካ ክፍለ ከተማ የምክር ቤት አባል በመሆን ተመርጬ መንግስትንና ህዝብን በማገልገል ላይ እገኛለሁ፡፡
ከ2002 ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም በቀድሞው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአሁኑ የአካባቢና ደን ሚኒስቴር ተቋም ውስጥ የለውጥና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በመካከለኛ አመራርነት ደረጃ ስመራና ከፍተኛ አመራሩን በልዩ እረዳትነትና በአማካሪነት ስደግፍ ቆይቻለሁ፡፡ የተቋሙ ራዕይ ማሳኪያ ተግባራት ውስጥ አንዱ በሆነው በAdaptation program ዘርፍ በተቋሙም ተወዳደርሬ በተቀጠርኩበት የስራ ዘርፍ በህጉርና በአለም አቀፍ ደረጃ በአየር ንብረት ለውጥ ድርድሮች ላይ አገሬን በመወከል በመደራደር ለ3 ዓመታት ፈር ቀዳጅ ውጤቶችን ካሲመዘገቡ አመራሮች ውስጥ አንዷ ነኝ፡፡ በዚሀ ተቋም የለውጥና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክተር ሆኜ ስመደብ ፤ በወቅቱ በተቋሙ የነበረው የተከማቸ የመልካም አስተዳደር ችግር እና ስር የሰደደ የኪራይ ሰብሳቢዎች ድርጊትና አስተሳሰብ ተቋማዊ ለውጡ ተግባራዊ እንዳይሆን በግልጽ ከፍተኛ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ከፍተኛ አመራሮችና ፈጻሚዎች የሚገኙበት ተቋም መሆኑን የጠቅላይ ሚ.ር ጽ/ቤትና ድርጅቱ/ኢህአዴግ በመረዳት ይህንን ደግሞ መምራትና ውጤት ማምጣት የምትችይው አንቺ ነሽ በማለት የሞት ሽረት ትግል ውስጥ እንድገባ ተልእኮ ተሰጥቶኝ በብቃትና በቅንነት ሀላፊነቴን ስወጣ ቆይቻለሁ፡፡
በተቋሙ የለውጥ ስራዎችን ስመራና በተደራቢነት የወቅቱ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተርን በልዩ ረዳትነትና አማካሪነት ስደግፍ ሳማክር በተቋሙ ውስጥ የለውጥ ጭላንጭል መታየት ሲጀምር ተቋሙ ከከፍተኛ አመራር እስከ ፈጻሚ በጥቅም ትስስር እና በብልሹ አሰራር የተዘፈቀ በመሆኑ ተቋማዊ ለውጡን ተግባራዊ በማድረግ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት መፍትሔ ለመስጠት የሚደርገው ከፍተኛ ጥረትና እልህ አስጨራሽ ትግል በኔ እና በጥቂት የለውጥ ሀይሎች ብቻ የሚገፋ አልነበረም፡፡ ተቋማዊ ለውጡ መመራት የሚገባው በከፍተኛ አመራሩ መሆን ሲገባው በተቀራኒው እራሱ ከፍተኛ አመራሩ የችግሩ አካል በመሆን የህዝብና የመንግስት አደራን ወደጎን በመተው በግል መበልጸግን እንደመብት የማየት አዝማሚያ እና አመለካከት እንደ ስርዓት በተቋሙ ውስጥ የበላይነት ያገኘ እና የተለመደ ጉዳይ ነበር፡፡ ይህ የጥቅም ትስስር በወቅቱ ማንም ሊነካው የማይደፍር ስለዚህ ጉዳይ አጀንዳ አድርጎ መታገል/አስተያየት መስጠት ከከፍተኛ አመራር እስከ ፈጻሚ የሚሰነዘር ኩርኩምና መሳደድን ለመቻል እራስን ማዘጋጀት የግድ የነበረበት ወቅት ነበር፡፡ ይህን የጥቅም ትስስር ሊያስቆም የሚሞክር ማንኛውንም እንቅፋት/ሀይል በረጃጅም ክንዳቸው ይደቆሳል ስራን እስከመልቀቅ ለሚመጣ አደጋ እራስን ማዘጋጀት የግድና የሁልጊዜ ትእይንት ነበር፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር በዚህ ሁኔታ ውስጥ ተቋማዊ ለውጡንና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን መምራት ምን ያህል ፈታኝ እንደሚሆን መገመት ይችላሉ፡፡ እኔም ድርጅቱና መንግስት የጣለብኝን ሀላፊነት ወደኃላ ሳላፈገፍግ በፍጹም ዲሞክራሲያዊና በብቃት እየተወጣሁ ቆይቻለሁ፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ አመራሩ በግልጽ የኢህአዴግ/የድርጅት አሰራርና እስትንፋስ በተቋሙ ውስጥ እንዳይኖር እንቅስቃሴ ቢታይም ማስቆም የየለት ተግባራቸው ነበር፡፡ እናም በከፍተኛ ጥረት ከጠ/ሚር ጽ/ቤጽ ጋር በመተባበር ም/ዋና ዳይሬክተሩ የድርጅት አባል እንዲሆን አራቱም ብሔራዊ ድርጅቶች እንዲቋቋሙ በመሆኑ የሀገሪቱ እና የድርጅቱ መሪዎች ድጋፍ እንዲያደርጉልኝ ጥሪ አቅርቤአለሁ፡፡ ይህም ተሳክቶ ከፍተኛ አመራሩ ተቋማዊ ለውጡ ውስጥ የመሪነት ድርሻውን እንዲወጣ አድርጌአለሁ፡፡ በዚህ ሂደት ምን ያህል በኔና በቤተሰቤ ላይ አስጊ አደጋ እንደተጋረጠብኝ እና ተቋማዊ ለውጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እልባት ለመስጠትና ለማሰጠት የሚደረግ ትንቅንቅን በጽናት በፍጹም የሀላፊነት ስሜት በብቃት ለመወጣት ሴትነቴ ሳያግደኝ የማደርገውን ጥረት እና እየታየ ያለውን የለውጥ ጭላንጭል አበረታች መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ጠ/ሚር ጽ/ቤት ሶስት ሚ/ር ዴኤታዎችን ከጽ/ቤቱ በመመደብ በቅርበት እንዲደግፉኝና ተቋማዊ ለውጡን በቅርበት እንዲከታተሉ ተመድበውልኝ በተቋሙ ውስጥ ሰፊ የለውጥ ስራዎች ተሰርተዋል አሰራርና አደረጃጀትን የሚለውጡ ሰፊ ጥናቶች ተደርገዋል ፡፡ በዚህ ሂደትም የተጀመረው ለውጥና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዳይቀለበሱ ከፍተኛ ጥረት ሳደርግ ቆይቼ ተጨባጭ የሆነ የአሰራር የአደረጃጀት ለውጦችና በማምጣት ተቋሙ ወደ ሚኒስቴር መ/ቤትነት ለማደግ በቅቷል፡፡ ተቋማዊ ለውጡም መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ሲጀምር ሂደቱ በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅማቸውን የነካባቸው አመራሮችና ፈጻሚዎች ለውጡን ለማደናቀፍ ምቹ ሁኔታ ሲጠብቁ ቆይተው የቀድሞ ጠ/ሚር ህልፈተ ሞትን ተከትሎ በቅርበት ለተቋማዊ ለውጡና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ሲደግፉኝ እንደነበር ስለሚያውቁ፤ ተቋሙን በቅርበት በመከታተል የሚያደርጉት ጥረት በመቋረጡ ምክንያት እኔን ጠልፈው ሲጥሉኝ ምንም ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ በተቋሙ ውስጥ ያለውን ስር የሰደደ የረጅም ጊዜ ብልሹ አሰራር የኪራይ ሰብሳቢነት የአመለካከትና የተግባርን አምርሬ በመታገሌኪራይ ሰብሳቢ በሆኑት በተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ግብራበሮቻቸው በደረሰብኝ ህገወጥ እና የመልካም አስተዳደር መርህ የጣሰ በደል ይፈጽሙብኝ ጀመር፡፡ ያለምንም ጥፋት በዲሲፕሊን እንድቀጣ፤ በወር ደሞዝ እንድቀጣ፤ በውድድር ካገኘሁት የስራ ደረጃዬ እና ደሞዜ ዝቅ ብዬ እንድሰራ በማድረግ የጠቅላይ ሚንስትሩን ህልፈት ተከትሎ ያሁሉ ተቋማዊ ለውጡ አደጋ የሆነበት ሐይል ድራሼን ለማጥፋት ቆርጦ ተነሳ፡፡ ይህን መነሻ በማድረግ ባለዉ ደንብና ሥርዓት መብቴን ለማስጠበቅ እና ፍትሕ እንዲሠጠኝ መጋቢት 2005 ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አመልክቼ ከ13 ወራት እና ከረጅም ጊዜ እንግልት በኃላ ጉዳዬ ተገቢ ትኩረት ተሰጥቶት ፍትህ ቢሰጠኝም፤ በሞት ሽረት ትግል ከፍተኛ አመራሮቹን ቸምሮ በፈጸሙት ደባና ህገወጥ የአሰራር ሂደትና በብልሹ አሰራራቸው ተገምግሞ ከነግብራበሮቻቸው ከአመራርነት ተባረው እርምጃ ቢወሰድባቸውም የቡድናቸውን የጥቅም ትስስር መንግስትና ድርጅቱ ሊየስወግድ ባለመቻሉ ዉሣኔዬ ተፈጻሚ ሊሆን አልቻለም እስካሁን አምስት አመት ሙሉ እኔና ቤተሰቤ በረጃጅም ክንዳቸው በየደረስንበት እንደቆሳለን፡፡ ሚዲያዎች የተፈጠረውን አስከፊ የመልካም አስተዳደር ችግርና የተወሰነልኝ ውሳኔ ተግባራዊ አለመደረግ የሀገሪቱ የፍትህ ስርዓት ምን ያህል ጥያቄ ውስጥ እንደገባ ቢዘግቡም ይህንን ጉዳይ የማያውቅ የድርጅትና የመንግስት ከፍተኛ አመራር ባይኖርም ማንም ግን መፍትሔ ሊሰጠኝ አልቻለም ጉዳዬ ሰሚ አጥቶ እቤቴ ቁጭ ብያለሁ፡፡
የተሰጠኝ ፍትሓዊ ዉሣኔ በሀገራችን ያለዉን ፍትሓዊና የፀና ሕገ መንግሥታዊ አስተዳደር የሚያመለክት በመሆኑ እኔም ሆንኩ የኔን ጉዳያ በሚድያ የሚከታተሉ የህ/ሰብ ክፍሎች/ ሚዲያዎች ቤተሰቤ የትግል አጋሮቼ እና ሁሉ በዉሣኔዉ ደስተኛ ነበርን፡፡ ሆኖም እጅግ በሚገርም እና በሚያሳዝን ሁኔታ ተቋሙ ፤ ወሣኔዉን ተግባራዊ ለማድረግ አሻፈረኝ በማለቱ በሀገራችን ያለዉን የሕግ የበላይነት ጥያቄ ዉስጥ አስገብቶአል፡፡ ቀደም ሲል በነበርኩበት ተቋም በደረሰብኝ ግፍና በደል መነሻነት በፐብሊክ ሚ/ር ተጣርቶ ከረጅም እንግልት በኃላ በተወሰነልኝ መሠረት ውሳኔዎች ሁሉ ሰዎች ከህግና ከህገ-መንግስ በላይ ሆነው አንዱም የተወሰነልኝ ውሳኔ ተግባራዊ ሳይደረግ ቀረ፡፡ የፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ሚኒስቴር በጥገኝነት ለሁለት አመት ካስቀመጠኝ በኃላ የወሰነው ውሳኔ ተግባራዊ አለመሆን ከኔ በላይ ሊያንገበግበውና ሊሰማው የሚገባው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴርና ከፍተኛ አመራሮች ሆኖ ሳለ Risk ወስደን ነው እዚህ ተቋም ያስቀመጥንሽ አርፈሽ ተቀመጪ አገር ምን ችግር ውስጥ እንዳለች ማወቅ አለብሽ ተብዬ በድጋሚ ለሁለት አመት እቤቴ ተቀምቼ ቀርቻለሁ፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር እኔ የማይጠየቁ የማይከሰሱ ሰዎችን ታግዬ እረትቼ ፤ ለተቋማዊ ለውጥ ስል selfless በመሆን የደረሰብኝ በደልና እየተፈጸመብኝ ያለው የመብት ጥሰት በህገ መንግስቱ አንቀጽ (:( ማንኛውም ሰው ለደረሰበት በደል አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፤ ቢልም እኔ ግን ለደረሰብኝ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥሰቶችን በህግ ጠይቄ የፍትህ ውሳኔ አግኝቼ ተፈጻሚ ሳይሆንልኝ በመቅረቱ እና ለተነፈግሁት ፍትህ እንዲደግፉኝ ስጠይቅ አብዛኛው የድርጅትና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንዲህ አይነት ችግር ውስጥ እንደገባሁ ማንን ተማምኜ እንድሆነ ሲጠይቁኝ እንዴት ደፍረሽ እንደዚህ ታሪካዊ ስህተት ትሰሪያለሽ በማለት እኔ እንደ ዜጋ በህግ ፊት እኩል የመዳኘት መብት እንደሌለኝ አምኜ እንድቀበል በሚገባኝ አገላለጽ እየነገሩኝ ያሰናብቱኛል፡፡ እናም በxውን እንዴት ብዬ ሁሉም ዜጋ በህግ ፊት እኩል ነው ብዬ ልመስክር እርሶም የኔን ጉዳይ አጥንተው አስተያየትዎትን በሀገራችን የፍትህ ስርዓቱ ምን ያህል አደጋ ውስጥ እንዳለ ያረጋግጡ፡፡ ሁሉም ከፍተኛ አመራር እኔ በድፍረት የገባሁበት የታገልኩትን የኪራይ ሰብሳቢዎችን ድርጊትና የተዛባ አመለካከት አድንቀው በስርዓቱ ውስጥ ተምሳሌት ነሽ ብለው ሲያበቁ በሀገሪቱ ውስጥ ፍትህ ለሁሉም ሰው እኩል እንደማይሰራና አምኜ እንድቀበል አስገድደውኛል፡፡ የሀገር መሪዎች የወሰኑልኝ ውሳኔ እንደዘበት ተረስቶ እነሱም ምንም እንዳልተፈጠረ ከጎኔ ሁነው እያዩ ማንን ተማምነሽ ነው ከነእገሌ ጋር ትግል የጀመርሽው እየተባልኩ መልካም ስሜ ሳይመለስ ለበደሉኝ ከፍተኛ አመራሮች ቦታ እየተቀያያረላቸው ከማን ፍትህ ልጠብቅ ከዚህ የበለጠ ለምን አይነት የመልካም አስተዳደር ችግርና መፍትሔ ይገኝ ይሆን ? ግራ ገብቶኝ በርሶና በእርሶ ብቻ ፍትህ ማግኘት እንደምችል ተስፋ በማድረግ ይህንን ደብዳቤ ለእርሶ አቅርቤያለሁ፡፡
ከግሌ ጥቅምና ምቾቴ ይልቅ በመንግስት ስራዬና በድርጅት የሚሰጡኝን ተልዕኮ ለማሳካት እስካሁን ያደረኩትን ትግልና ያሳየሁት ቁርጠኝነት በድጋሚ በፐ/ሰ/ሰ/ሀ/ሚንስቴር በጥገኝነት ባስቀመጠኝ ወቅት ባሳየሁት ለአገራዊ ተቋማዊና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዲሁም ለተቋሙ አሁን ላለበት የአደረጃጀት እና የአሰራር ለውጥ በማንኛውም ደረጃ ላይ ላለ አመራርና ፈጻሚ ተምሳሌት መሆን እንዳለበት በሰራተኞች መድረክ በክብርት ም/ጠቅላይ ሚንስቴር እየመሰከሩ፤ በግንባር ቀደምንት እየሸለሙኝ የደረሰብኝን የመልካም አስተዳደር ችግር ግን እስከመጨረሻው ሳይቋጩልኝ የበደሉሽ የህወሓት አባለት ናቸው ሄደሽ ለዶ/ር ደብረጽዮን ንገሪው ተብዬ ቢሮአቸው በር ላይ ስንከራተት ከርሚያለሁ። አምስት አመት ሙሉ እከሌ/እከሊት ጋር ሂጂ እየተባልኩ እየተንከራተትኩ አምስት አመት ሙሉ ፍትህ አጥቼ ተንከራትቻለሁ፡፡

በሌላ በኩል ግን ከፍተኛ የስነ-ምግባር ጉድለት ያለባቸው በመንግስት ስራ ሰዓት በሀሰተኛ የአማካሪነት ፍቃድና በህገወጥ ቲተር ከመንግስት መ/ቤት ውጪ የማይሰሩ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ስራዎችን እየሰሩ ያልተገባ ጥቅም ሲያገኙ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ወንጀሉን መፈጸማቸውን አምነው የተቀበሉ ግለሰቦች ደፋ ቀና የምልበትን ተቋማዊ ለውጥ ከማደናቀፍ ባሻገር ያለምንም ጥፋቴ በሁለት ወር ደሞዝ እና በከፍተኛ የዲሲፕሊን ቅጣት በውድድር ካገኘሁት የስራዬ ደረጃዬና ደሞዜ እነዚህ ወንጀለኞች አባረውኛል፡፡ በፍጹም በዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ ያለች ሀገር ውስጥ ይፈጸማል ተብሎ የማይገመት የፍትህና የመብት ጥሰት የሀገሪቱን የሲቪል ሰርቪስ መተዳደሪያ የህግ ድንጋጌ (Legislative decree ) በጣሰ ሂደት እኔ ከስራዬ በነዚህ ህገ ወጥ ግለሰቦች ተባርሬ ከ13 ወራት በኃላ መንግስትና ድርጅቱ፣ ሚዲያዎች ጥልቅ ምርመራ በማድረግ የደረሰብኝ ጥቃትና እንግልት ለተቋማዊ ለውጥና ለመልካም አስተዳደር ስራዎች ተልኮዬን ባግባቡ ስወጣ ጥቅማቸው የተነካባቸው አመራሮች ሆን ብለው ያቀናበሩት መሆኑ በከፍተኛ የሲቪል ሰርቪስ ሚ/ር አመራሮችና ባለሙያዎች ተረጋግጦ ወደ ስራዬና የስራ ደረጃዬ እንድመለስ፤ ይህንን እርምጃ በወሰዱብኝ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ተደጋጋሚ ደብዳቤ ቢጽፍም ውሳኔው ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ውሳኔው በሁለት የሀገሪቱ ም/ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና በሶስት ሚንስት ዴኤታዎች የተወሰነ ቢሆንም የአካባቢና ደን ሚ/ር ሚንስትር ግን እሲኪ ማን እንደሚያስፈጽመኝ አያለሁ ብለው እንደፎከሩት ጉዳዬ ተፈጻሚ ሳይሆን ተንጠልጥሎ ቀርቶአል፡፡ በቀድሞ ሁለት የሀገሪቱ ም/ጠቅላይ ሚንስትሮች እና የፐ/ሰ/የሰ/ሀብት ልማት ሚንስትሮች ስልጣን እና በሀገሪቱ የሲቪል ሰርቪስ ህግና ደንብ ተከትሎ የተወሰነልኝ ውሳኔ ደብዳቤ ቅርጫት ውስጥ ተወርውሯል፡፡ እነሱም እንሀገር መሪ ወስነውልኝ ተግባራዊ ሳይደረግ መቅረቱን እያወቁ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ፍትህ ነፍገውኛል፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት የዲስፕሊን እርምጃ እንዲወሰደብኝ የተመደበውና የዲስፕሊን እርምጃ የወሰደብኝ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ በፖሊስ ተይዞ በፍርድ ቤት ውሳኔ እስር ቤት ቢገባም በግብራበሮቹና በአመራሩ እረጅም እጅ ለተወሰኑ ወራት ታስሮ በአመክሮ እንዲወጣ ተደርጎ የደረጃ እድገት ተሰጥቶት በተቋሙ ሲመደብ እኔ ያለምንም ጥፋቴ የወሰዱብኝ እርምጃ በሁለት የሀገር መሪዎች የተወሰነልኝ የፍትህ ውሳኔ ተግባራዊ ሳይሆን ወደ ስራ ደረጃዬ ሳልመለስ ቀርቷል፡፡
በተቋሙ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ብልሹ አሰራርን ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግርና የመንግስት ሀብት ብክነትን የለውጥ ዳይሬክተር በመሆኔ ለማስተካከል ስታገል የደረሰብኝን በደልና አስተዳደራዊ የህግ ጥሰት የተለያዩ ሚዲያዎች ይፋ ማድረግ ሲጀምሩና፤ በተለይም የዛሚ ራዲዮ ጣቢያ ሰፊ ጥናት ካደረገ በኋላ ባዘጋጀዉ የቀጥታ የሬድዬ ውይይት ላይ ጋብዘዉኝ ተገኝቼ የተሳተፍኩ ሲሆን ህዝቡን ባሳተፈ ሁኔታ በተሠራዉ የቀጥታ የሬድዮ ፕሮግራም በቂ መረጃ ከህዝቡና ከጋዜጠኞች በተደረገ ተጽዕኖ መንግስት የመፍትሔ እርምጃ ወስዷል፡፡

የአካባቢና ደን ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ፈጻሚዎች ላይ መንግስት በወሰደው እርምጃ ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ ተቋሙ በእኔ ላይ የፈጸመዉ በደል ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር ያለበት ፍትሀዊ ያልሆነ መሆኑ በመረጋገጡ፤ በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚ/ር ፡ የሲቪል ሰርቪስ ከፍተኛ አመራሮችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አራት ዳይሬክተሮች ያሉበት ቡድን ተቋቁሞ ጉዳዩን በዝርዝር ከመረመረ በኋላ ከ13 ወራትእንግልት በኋላ ወደ ስራዬና የስራ ደረጃ እንድመለስ እና የ13 ወራት ደመወዜ እንዲከፈለኝ ወስኖልኛል፡፡
ሚዲያዎች ተከታትለው የዘገቡት የኢህአዴግ እና የመንግስት ባህሪው ባልሆነ ፍፁም ፀረ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ማመን የሚከብድ የደረሰብኝ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግርና የመብት ጥሰት በህገመንግስቱ አንቀጽ (( 🙁 ማንኛውም ሰው ሰብአዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው ተብሎ ቢደነገግም ምንም ባላጠፋሁት ጥፋት ተወንጅዬ የተወሰደብኝ እርምጃ ትክክል አለመሆኑንና የበደል በደል ህገወጥ የመብት ጥሰት መሆኑ ይህም እንዲስተካከልና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ቢወሰንልኝም በሚዲያ ቢነገርም መልካም ስሜ ሳይመለስልኝ ቀርቷል፡፡እንዲሁም በህገ መንግስቱ በአንቀጽ (( ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን የእኩልነት መብትን በተመለከተ “ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በህግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ በዘር፣ በብሔር፣ብሔረሰብ፣ በቀለም፣በፆታ በቋንቋ፣ …. ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የህግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው ይላል” ይህ አንቀጽ ግን ለእኔና ለሁለት የሀገሪቱ ም/ጠ ሚንስትሮች ሳይሰራ ቀርቶ አንድ ወንጀለኛና ተባባሪው የአካባቢና ደን ሚንስቴር ሚንስትር ግን ከእስር ቤት እንዲወጣ ተደርጎ በክብር የደረጃ እድገት ተሰጥቶት ስራው ላይ ሲመደብ እኔ ለፍትህና ለዲሞክራሲ ልእልና ለተቋማዊ ለውጥ ስዋትት በእሱና የጥቅም ተጋሪዎቹ ተጠልፌ ወድቄ ከአመት በኃላ ያገኘሁት ፍትህ እንደዋዛ ተጥሎ ፐብሊክ ሰርቪስ ሚኒስቴር በጥገኝነት ስራ እየሰራሁ ደሞዝ እያገኘሁ የውሳኔዬን አፈጻፀም እንድከታተል ለተወሰነ ጊዜ ካስጠጋኝ በኃላ Risk ወስዶ እንዳስቀመጠኝ ነግሮኝ አሸማቆኝ ሁሉን ነገር ትቼ እቤቴ ተቀምጫለሁ ፡፡
ይህንንም አሁን በስልጣን ላይ ላሉት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚንስትር ክቡር አቶ ታደሰ ጫፎ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ የደረሰብኝን የመልካም አስተዳደር ችግሮቼን ነግሬ ሰምተው ካበቁ በኃላ በደብዳቤ ጠይቂኝ እንኳን አንቺ አይደለም ስንቱ እስከነ ችግሩ ስራ እንዲሰራ ተደጋጋሚ እድል ይሰጠዋል ብለውኝ ማመልከቻዬን በጽሑፍ አቅርቤ አንዴ አንብበውት ለባለሙያ ወርውረው ደግመው አላዩትም አመት ሙሉ መልስ አልሰጡኝም፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር የደረሰብኝን በደልና የመብት ጥሰት ወደፍትህ በማምጣት ከረጅም ጊዜ እንግልት በኃላ ተወስኖልኝ ፍትህ ባገኝም፤ ከሀገሪቱ የህጎች ሁሉ የበላይ በሆነው ህገ-መንግስት በአንቀጽ (:( “ሁሉም ሰዎች በሕገ ፊት እኩል ናቸው” በመካከላቸውም ማንኛውም ልዩነት ሳይደረግ በህግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል የሚለው አንቀጽ ለእኔና ፍትህ ለነፈጉኝ አካላት ምን ትርጉም ይሰጠው ይሆን? እርሶስ በሀገሪቱ ውስጥ የህግ የበላይነት እና ሰዎች በህግ ፊት እኩል ይዳኛሉ ብለው ያምናሉ? ሁሉም ከፍተኛ አመራር/ወይም ዜጋ በህግ ፊት እኩል ስልጣንና ተሰሚነት አላቸው? ቢኖራቸውማ በሁለት ም/ጠቅላይ ሚኒስትሮች የወሰኑት ውሳኔዬ ሁለት ጊዜ ተጽፎ የአንድ ተቋም የስራ ሀላፊ እንዴት ውሳኔውን አልቀበልም ይላል? በተቃራኒው ግን እኔን ያለምንም በደሌ ከስራ ደረጃዬ እና ከደሞዜ ተፈናቅዬ ስቀር በዚያው ሳምንት የኔን ውሳኔ አልቀበልም በተባልኩበት ሳምንት ውስጥ በወንጀል ተቀጥተው እስር ቤት እያሉ የደረጃ እድገት እንዲያገኙ ተደርጎ የስራ መደባቸው ክፍት ሆኖ ጠብቋቸው ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ እናም እኔ የት ሔጄ ፍትህ ላግኝ ሌላ አገር የለኝምና? የሔድኩባቸው ከፍተኛ የድርጅትና የመንግስት ሀላፊዎች ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ እየሰጡኝ እንዴት እንደዚህ አይነት ችግር/ትግል ውስጥ ገባሽ ሞኝ ነሽ ሁሉም በመድረክ የሚባለውና የሚጻፈው እውነት ይመስልሻል ተሞኘሽ በማለት ማንም መፍትሔ ሊሰጠኝ እንደማይችል ይነግሩኛል፤ እናም አንገቴን ደፍቼ የሰው/የቤተሰብ ጥገኛ ሆኜ ቤቴ ቀርቻለሁ፡፡
እናም ክቡርነትዎ፡- ያለኝ አገር አንድ ነውና በሀገሬ ህግ ደንብ መሰረት ፍትህ አግኝቹ በሀገሬ ሰርቼ እንድኖር እንዲያደርጉኝ እና ከ20 አመት በላይ በመንግስት ስራ እየሰራሁ ሀገሬን ቤተሰቤን እየደገፍኩ እራሴን ከማስተዳድርበት የመንግስት ሰራዬ ላይ በተቀነባበረ ደባ ወቅቱ በሚደግፋቸው ከህግና ከህገመንግስቱ በላይ በሆኑ ቡድኖች አምስት አመት ሙሉ ስንገላታ መቆየቴን ተረድተው ፍትህ እንዲሰጡኝ በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር !
ግልባጭ
ለኢህአዴግ ጽ/ቤት
ለክቡርዶ/ርአዲሱየኢፊዲሪሰብአዊመብትኮሚሽንኮሚሽነር
አዲስ አበባ