የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት ከቤኒሻንጉል ለተፈናቀሉ አማራዎች የ30 ሺ ብር ድጋፍ አደረጉ ።

“ከገንዘብ በላይ ልብ ነው ይዘን የመጣነው!” የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት አታላይ ዛፌ፣ አለነ ሻማ፣ ጌታቸው አደመ እና እነ አክቲቪስት ንግስት ይርጋ ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉ አማራዎችን ጠይቀዋል፣ ወገናዊ መልክትም አስተላልፈዋል። የ30 ሺ ብር ድጋፍም አድርገዋል።

“ከገንዘብ በላይ ልብ ይዘን ነው የመጣነው!” ብለዋል አቶ አታላይ ዛፌ