አማራዎችን ማፈናቀል ቀጥሏል። ከኦሮሚያ ክልል ኢሊባቡር አካባቢ አማራዎች ተፈናቀሉ።

አማራዎችን ማፈናቀል ቀጥሏል። ከኦሮሚያ ክልል ኢሊባቡር አካባቢ አማራዎች ተፈናቀሉ።ከኦሮሚያ ክልል ኢሊባቡር አካባቢ ከተፈናቀሉት አማራዎች መካከል 60 ያህል በአሁኑ ወቅት ባህርዳር ክልል አስተዳደር ቢሮ እንደሚገኙ ታውቋል።

ኢሉ አባቦራ፣ በደሌ/77 ከሚባል ቦታ የተፈናቀሉት አማራዎች

ባህርዳር የሚገኙት 64 ግለሰቦች ብቻ ናቸው። ቤተሰቦቻቸው ተበትነዋል!

ቤታቸው ተቃጥሎባቸዋል። ንብረታቸው ተወርሷል። ወድሟል።

የተገደለ፣ እጁን የተቆረጠ እና ቤቱ ውስጥ የተቃጠለም እንዳለ ተፈናቃዮቹ ገልፀዋል

ከአካባቢው የተፈናቃሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ሲሆኑ የአካባቢው የመንግስት አስተዳደር ምንም አይነት ጥበቃ ወይንም እገዛ አላደረገላቸውም። እንዲያውም እንዲፈናቀሉ እያደረገ ያለው የአካባቢው የመንግስት/ኦህዴድ መዋቅር እንደሆነ ገልፀዋል።

ባህርዳር የገቡት ዛሬ 13/2010 ዓም ሲሆን ብአዴን የባህርዳር ጎዳናዎች ላይም እንዳያድሩ በፖሊስ እያስነሳቸው ነው።

ከመጋቢት 7/2010 ዓም ጀምሮ ከአካባቢው ከ3 ሺህ በላይ ነዋሪዎች እንዲወጡ መደረጉን ተፈናቃዮቹ በስልክ ገልፀውልኛል። የባህርዳር ሕዝብ ከቤንሻንጉል ለተፈናቀሉት እንዳደረገው አኩሪ ተግባር ከኦሮሚያ የተፈናቀሉትንም እገዛ እንደሚያደርግላቸው ይጠበቃል።

ከኦሮሚያ ኢሉ አባ ቦራ ተፈናቅለው ባህርዳር የገቡትን አማራዎች የክልሉ ፖሊስም ከተቀመጡበት እያስነሳቸው ነው።የባህርዳር ሕዝብ እና ቤተ ክርስትያን መጠለያ ካልሆኗቸው የብአዴን ነገርም የታወቀ ነው።የባህርዳር ሕዝብና ቤተ ክርስትያን ከለላ ካልሆኗቸው ብአዴን አዳሩን ወዳልታወቀ ቦታ እንደሚወስዳቸው ግልፅ ነው!

Image may contain: one or more people, people standing, sky and outdoor

ከኦሮሚያ ኢሉ አባ ቦራ ተፈናቅለው ባህርዳር የገቡትን አማራዎች የክልሉ ፖሊስም ከተቀመጡበት እያስነሳቸው ነው