ቤተ ክርስትያንም በወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት ጉዳይ ገብታለች!

ዳንሻ ነው። እነ ቄስ ሙሉ በአማርኛ በመስበካቸው ወንጀል ሆኖባቸዋል። በዚህ ከተማ በሚገኝ ቤተ ክርስትያን አንድ የትግራይ ጳጳስ መጥተው በትግርኛ ሲሰብኩ ህዝብ “በአማርኛ ነው የምንፈልገው” ይላል። እነ ቄስ ሙሉ “እናንተ ናችሁ እንዲህ የምታደርጉ” ተብለው ይታሰራሉ። ከፖለቲካ እስራቸው በተጨማሪ ቤተ ክርስትያንም ሌላ የፖለቲካውን ክስ ማክበጃ የሀይማኖት ክስ ጨምራባቸዋለች። እምነትም በማንነት ጉዳይ ገባች። ቤተ ክርስትያን በቀሳውስቱ ላይ ያስተላለፈችውን አሳዛኝ ብይን አንድ ወዳጄ ተርጉሞ ልኮልኛል።

……Getachew Shiferaw…………………………

በኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ሀገረ ስብከት የዳንሻ ወረዳ ቤተ ጽ/ቤት

ዳንሻ

ለ መምህር ሰለሞን አቡሆይ

ጉዳዩ በወረዳው ሀገረስብከት ና ጠ/ቤተክህነት የተናገራችሁት የስም ማጥፋት ይመለከታል።

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው እርስዎ በቀን 17/01/2010 ዓ/ም በደ/ቅ/አ/አረጋዊ በተዘጋጀው ግብዣ ተገኝታችሁ በምረቃው ግዜ የወረዳው ሀገረስብከትና ጠ/ቤተክህነት ተሃድሶ ሆነዋል፣11 መምህራን ተባረዋል። እኔ የማላውቀው የለም። ብላችሁ መናገራችሁ ሰምተን ጠርተናችሁ የተናገራችሁትን “እኔ ተሃድሶ አላልኩም። ከደ/ሳህል ከምንለያይ ጀምሮ ምን ሆነን ነው የተለያየን ሰበካ ጉባኤውም ምን ሆኖ ተበተነ? እንደ ኢትዮጵያና ኤርትራ፣ደ/ሱዳንና ሰ/ሱዳን ነው የሆነው። ለምን አንፋቀርም? በሚል ብቻ ነው ያስተማርኩት እንጂ ሌላ ያልኩት የለም ይሄንን ግን ዲያቆናቱና ካህናቱ ወደ ሌላ ነገር ተርጉመውት ሊሆን ይችላል ነው ያላችሁን። ምስክሮች ቀርበው በሰጡት ምስክርነት ከ8 ምስክሮች 6ቱ በወረዳው ሀገረስብከትና ጠ/ቤተክህነት ተሃድሶ አሉ ማለታችሁ አንዱ ደጋግመው ተሃድሶ ይሉ ነበር ለማን እንደሆነ አላስተዋልኩም ሲሉ ሌላኛው ደግሞ ተሃድሶ ያሉት ለሰበካ ጉባኤው ነው ሆኖም ግን ደጋግሞ ተሃድሶ እያለ ነበር ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

ምስክርነቱን ከተቀበልን በኃላ እንደተባለው ወደ ወረዳውም የጠራናችሁ የስም ማጥፋት ስራ እንዳደረጋችሁ ለወረዳው ይሁን ለሀገረ ስብከቱና ጠ/ቤተክህነቱ ተሃድሶ ማለታችሁን አረጋግጠን ወደዚህ ውሳኔ ገብተናል።

በመሰረቱ ከላይ የተዘረዘረው ጥፋት እና ደግሞ በኃይማኖት መሪዎች የተሃድሶ ሃይማኖት ሆነዋል ብለህ ማረፍ ለተመሪው ምእመናንና ህዝብ፣ጠቅላላ ቤተክርስቲያን ከነመሪዎቿ እንድትለይ የሚያደርግ መሰረት የሌለው የስም ማጥፋት ዘመቻ እና ደግሞ ብዙ ሰው በተሰበሰበበት መናገር ከባድ ቢሆንም እኛ የወረዳው ቤተክህነት ከጥፋታችሁ ትመለሳላችሁ ትማራላችሁ የምትናገሩትን ታስተውላላችሁ በማለት ምንም ከባድ ቅጣት የሚያስከትል ቢሆንም እንኳ የ6 ወር ከደሞዝና ከአግልግሎት እንድትታገዱ ቀጥሎ ደግሞ ከ6 ወር ቀጥሎ የሀገረስብከት ድጋፍ እስከዛሬ ስላላመጣችሁልን የድጋፍ ደብዳቤ ይዛችሁ መመጣት እንዳለባችሁ ካለመጣችሁ ግን ወደስራችሁ መመለስ እንደማትችሉ በመስማማት በአንድ ድምፅ ወስነናል።

መ/ፀ ሙሉ ድረስ ሊቀ ካህናት
መ/ታ ፍሬው ተወልደ ሰ/ጉባኤ/መ/ዋ
መ/ሳህል አየልኝ አበራ ግምጃ ቤት
ቄስ ገ/ሚካኤል አስመላሽ ሰ/ት/አደራጅ
ቄስ መንግስቴ ብርሃነ ፀሓፊ

No automatic alt text available.

No automatic alt text available.