ትረምፕ “ተሰልዬ ከነበረ ይጣራልኝ” አሉ

የዛሬ ሁለት ዓመት በተካሄደው የዩናየትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት የፖለቲካ ተነሣሽነት የታጀበ ስለላ በምረጡኝ ዘመቻ ቡድናቸው ላይ ተካሂዶ እንደሆነ እንዲጣራላቸው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባሳደሩት ጫና የፍትሕ መሥሪያ ቤቱ ጠቅላይ መርማሪው ሁኔታውን እንዲያይ መጠየቁን አስታወቀ።