የኢትዮጵያ መንግስት ሰንዓ በሚገኘው የሚሲዮኑ ፅ/ቤት አማካኝነት ጉዳዩን በመከታተል ላይ መሆኑ ሲታወቅአደጋውን በተመለከተም አዲስ አበባ የሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ የተሟላና አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲያቀርብ መንግስት መጠየቁን ጽ/ቤቱ ባወጣው መግለጫ አውስቷል፡፡

መግለጫው በቅርቡ በየመንና በአካባቢው በተፈጠሩ ግጭቶችና ቀውሶች ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን መንግስት ወደ አገራቸው የመለሰ መሆኑን አስታውሶ

ቀሪዎቹን ዜጎቻችንን ከየመን ለማስወጣት ከሳዑዲ መንግስት ጋር በመተባበር የተጠናከረ ጥረት በማድረግ ላይ ባለበት ወቅት ይህ አደጋ መከሰቱ መንግስትን እጅግ ያሳዘነው መሆኑን አስታውቋል፡፡

መንግስት በደረሰው አሰቃቂ እና አሳዛኝ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች፣

ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ መጽናናትን መመኘቱን መግለጫው አክሎ አስታውቋል