ኢሕአዴግ የፖለቲካ የበላይነቱን የኦሮሞ ድርጅቶች እንዲቆጣጠሩት በጋራ እቅድ እየነደፈ ነው።

ኢሕአዴግ የፖለቲካ የበላይነቱን የኦሮሞ ድርጅቶች እንዲቆጣጠሩት በጋራ እቅድ እየነደፈ ነው።

የሕወሃት የበላይነት በኢኮኖሚ መፈርጠሙን ያረጋገጠው ኢሕአዴግ በኦሕዴድ እና በኦነግ የፖለቲካ የበላይነት ሃገሪቷን ለማስተዳደር ማቀዱን ምንጮች ይጠቁማሉ። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መሾምን ተከትሎ በፈጠነ መልኩ ከኦነግ ሰዎች ጋር ድርድር መካሔዱ ኢሕአዴግ ባቀደው ቀጣይ የ አገዛዝ መስመር ላይ የኦሮሞ ፓርቲዎች አድራጊና ፈጣሪ ሆነው በፖለቲካ የበላይነት እንዲወጡ የሚደረግ ሒደት መስተካከሉና በውይይት ቀጣይ ስራዎች ሊስሩ እንደሆነ ተጠቁሟል። ለሕዝቡ እርባና የለሽ ነገር ከመፍጠር ውጪ ምንም ለውጥ አያመጡም። ኢሕአዴግ ከስሩ ተነቅሎ ካልተወገደ በቀር በኢትዮጵያው ውስጥ ታሪክ ላለፉት አመታቶች ራሱን እየደገመ ኢሕ አዴግ አፈር ልሶ እየተነሳ እያየን ነው። ለሕዝብ ጥቅም መቆም ማለት የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ ከድርድር ጀምሮ መታገል ነው። ፖለቲካው በ አጭበርባሪነትና እና በሽፍጥ በሴራና በተንኮል የተሞላ እስከሆነ ድረስ የኢሕ አዴግን እድሜ ከማስረዘም ውጪ ምንም አይፈይድም። ሕዝባዊ መንግስት ለመትከል መጀመሪያ የሽጝር መንግስት ማቆም ያስፈልጋል።

ከዚህ ውስጥ እንደ ኦፌኮና ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች የተወሰነ ድርሻ እንዲኖራቸው ቢደረግም በበላይነት የሚመሩት ግን ኦሕዴድና ኦነግ ናቸው። ኢነግ ስሙን ቀይሮ ኦዴፍ ቢልም ምንም አይነት ከህወሃት የተለየ አስተሳሰብ የሌላቸው እና ከሕወሓት ጋር ያደጉ አዛውንቶች ወደ ሃገር ቤት መግባታቸው ታውቋል።

አቶ ሌንጮ ለታ (የኦነግ መስራችና ፀሀፊ)የነበሩ
ዶ/ር ዲማ ናጎ (የኦነግ ሊቀመንበር)የነበሩ
ዶ/ር በያን አሶባ (የኦነግ ቃል አቀባይ)የነበሩ
ዶ/ር ሀሰን ሁሴን (የኦነግ አመራር አባል)የነበሩ
አቶ/ሌንጮ ባቲ (የኦነግ ቃል አቀባይ)የነበሩ።

የኦሕዴድ የፖለቲካ የበላይነት የሕዝቡን አመጽ እንደሚያከሽፈውና ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንዳሉት የይቅርታና የፍቅር እንደምታው የኢሕ አዴግ ዘራፊዎችናን ገዳዮችን ለማዳን የሚካሔድ ሂደት እንደሆነ ታውቋል። በሕግ ፊት ገዳዮችና ዘራፊዎች እንዳይጠየቁ ኢሕአዴግ የራሱን ገበና በይቅርታ ስም ሸፍኖ ለማሳለፍ የሚሰራው ሻጥር እንደሆነ ተገልጿል።

ኢሕአዴግ መደራደር ቢፈልግ ከሁሉም ስደተኛ ተቃዋሚዎች ጋር ሆኖ ኦዴፍን ብቻ መምረጡ ጥያቄዎች አስነስቷል። ሆኖም ኢሕአዴግ በእቅዱ መሰረት የሕወሓትን የኢኮኖሚ የበላይነት ጠብቆ ለማቆየት የኦሕዴድን የፖለቲካ የበላይነት መመስረት እንደ እቅድ ስለያዘው ለዚሁም የኦሮሞ ድርጅቶችን ያሳተፈ የሚል ሽፋን በመስጠት እድሜውን ለማስረዛም እየተጣደፈ መሆኑ ታውቋል።