የ80 000 ቶን አርማታ ብረት ያለቀረጥ ገብቶ መንግስት 3. 4 ቢሊዮን ብር አጣ!! ማን ጠያቂ ማንስ ተጠያቂ ?

የ80 000 ቶን አርማታ ብረት ያለቀረጥ ገብቶ መንግስት 3. 4 ቢሊዮን ብር አጣ!! ማን ጠያቂ ማንስ ተጠያቂ ?

በትግራይ ክልል 280 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ግንባታ ማስፈጸምያ ያለቀረጥ ከውጭ ሀገርየአርማታ ብረት ለማስገባ ከቀረጽ ነጻ ፍቃድ ይሰጠን ብለው ጠይቀው በወይዘሮ ምህረት የተባለች የትግራይ ገቢዎች ባለስልጣን ወይዘሮ አስቴር እንደሆነች የፈቀደች የሚናገሩ ከገቢዎች ቢሮ የሚመነጩ መረጃዎች ይናገራሉ ።

ያለቀረጽ የገባ የአርማታ ብረት በሙሉ ወደ ግንባታ ሳይውል ወደ ቸርቻሪ ነጋዴዎች በውድ ዋጋ ተሽጦ ቸርቻሪዎችም ለተጠቃሚ ህዝብ እጅግ በውድ ዋጋ እንደተሸጠ የክልል ትግራይ ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ይጠቁማሉ ።

ከላይ የተጠቀሰው መረጃ የሰማ የትግራይ ኢዚአና ተለብዥ ጋዜጠኞች የሙስናው መረጃ አነፍንፈውና አድነው መረጃ አሰባስበው ጉዳዩ በሚዲያ ሊያጋሉጡ ለገቢዎች ባለስልጧና ወይዘሮ ሊጠዩቋት ሲሄዱ ወይዘሮ በእግራቸው ወድቃ ስትለምናቸው ፣ ጋዜጦኞች ግን የወይዘረዋ እንበተኝነት እና ልመና የተባለው መረጃ ይዘው ወደ ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ ሄደው ሲነግሩት ደጉተሩ በግዜው እምላቹ ነገር ቢኖር በፍጥነት ዘግቡት አትስሟት ብሎዋቸው ሲያበቃ ። ደጉተሩ ግን ረጅም ጊዜ ሳይቆይ ለወይዘረዋ አትስሟት ብሏቸው የነበረው ቃሉን በማጠፍ የገቢዎች ባለስልጧና ሄዳ በእግሩ ወድቃ ደበቀኝ ደብቀኝ አታጋልጠን ካለቹ በኃሏ ፣ቆዬት ብሎ ለሚዲያዎች ጠርቶ ተውት የሚጣራ ነገር ስላለ አታሳራጩት ብሎዋቸው ፣ሚዲያዎችም ሊያሳራጩት ያሰቡት ወይ አዛጋጅተውት የነበሩ መረጃ አጥፈው እንደአስቀመጡት ምንጮቹ ይናገራሉ ። ታድያ ደክተር አዲስ አለም ባሌማ መጀመሪያ ለገቢዎች ሃላፊዋ አጋሉጧት ብሎ ሲያበቃ ኃላ ሀሳቡ ቀይሮ ማጋለጡ ለምን አቆመው ??ይህ ጥያቄ ለኢትዮጱያ አገር ወዳድ ወገኖች ልተዎው ። ሌላ ግን ደጉተሩ በሙሱና መመታት ያለው አቋም የላላ መሆኑ እና ምን ያህል ሀገራዊ ሀላፍነት እንደሌለው ካሀዲ እንደሆነ ያመለክታል ።
ቀረጽ ሳይከፈልበት ገብቶ ተሸጦ የሚባለው የአርማታ ብረት በዋናነት አብዛኛው የ9 ትጃሮች እንደሆነ የሚናገሩት ምንጮች ከ9ኙ ደግሞ በዋናነት አብዛኛው አርማታ በመቀለ የሚገኙ ከህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ የጠበቀ ቁርኝት እና የጥቀመኝ ልጥቀምህ የሚል ግንኝነት እንደነበራቸውና እንዳላቸው ምንጮች ይጠቁማሉ ።

ሁሉም ዜጎች ማስነሳት ያለባቸው ጥያቄ መመለስ ያለበት 1–ደኩተር አዲስአለም ባሌማ የ3 .4 ቢሊዮን ብር የክልላችን ገቢዎች ቢሮ ሀላፊዋ እዳትጋለጥ መደበቁ ምን አይነት ጥቅም ስለተካፈለ ነው ? ለመሆኑ ደጉተሩ ሀገራዊ ፣ዜግነታዊ ፍቀርስ አለው ወይ ??ይህሰውዬ ከልላችን ሊመራና በሀገር ደረጃ ይመራን ብብሎ ማን ያምነዋል ?
2 — ዶክተሩ የገቢዎች ሀላፊዋ ወይዘሮ እንዳትጋለጥ አድርጎታል በም በስንት ብር ልትጠቅመው ተስማምታ ነው የታረቁ ?
3—-ሚዲያዎች ደጉተር አዲስአለም ባለማ ሙሱና አጋልጠው ወይዘረዋ እዳትጋለጥ ሲያደርግ ለምን ይፈራሉ ?የሀገር ሀብት የወረሩ ሌቦች ለመጋለጥ እንዳይችሉ ለሌቦች ዘበኛ ሆኖ ዶክተር ሲከለክላቸው እሱን ረግጠው ለምን አያጋሉጡም ? ቢባረሩ ቢገደሉ ?የጋዜጠኛ ሀላፍነት አይደለም ? ጋዜጠኛ እኮ የህዝብ ሀላፍነት ይዞ በጦርኖት ነበልባል ገብቶም ይሰዋል ፣የኛ ጋዜጦኞች ከሌባ መሪዎች ለምን ለህዝብና ለሀገራችን ሀብት ማስቀደም አይሻልም ?
4 — የክልላችን አገር ውስጥ ድህንነት የፖሊስ ምርመራ አዛዞች ለተፎካካሪ ፓርት አመራር ፣ አባላት ፣ደጋፊዎች በገቡበት እየገባችሁ እንደባእድ እየተመለከታችሁ ስትወነጅሉ ትውላላችሁ ለሙሶኞች ፣ለሌቦች ግን እያጀባችሁ ትኖራላችሁ ?እንተስ የሀገርና የህዝብ ጥቅም ለመረጋገጥ ለምን አትጥሩም ? ለመሆኑ የኢኮኖሚ ፣ የጸጥታ ድህንነት ጥበቃ የሚባል ስራ ይገባችኃልን ?
5 የአርማታ ብረት ያለአገባብ ገብቶ በሌቦች እየተቸበቸበ እንዳለ ይህ ሌብነት የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ለሌቦች እርምጃ መውሰድ አያውቅም ማለት ነው ?
ለነገሩ የህወሓት መሪዎች ባለፉት 2 አመት ሙሱና ኪራይ ሰብሳቢነት ከግንዱ እንቆርጠው አለን እያለ ዲስኩሩ ሲያሰማን ከርሞ ነበር ። ነገር ግን በመጨረሻዋ ሰአት ሙሱና የሚባል ሳይነኩ ሸውደው እንደወጡ ሁሉ ህዝብ ያውቀዋል ስለዚህ አዲስ መድረክ እየከፈታችሁ አትሸውዱን ።
ከአስገደ ገብረስላሴ
መቀለ
14 / 09 / 2010