‘በሞያሌ ከተማ የተፈጸመው ግድያ በስህተት የሆነ አይደለም’ ሲሉ የተናገሩት የኦሮሚያ ከፍተኛ ባለስልጣን ታሰሩ ።

የኦሮሚያ ከፍተኛ ባለስልጣን ታሰሩ ።

‘በሞያሌ ከተማ የተፈጸመው ግድያ በስህተት የሆነ አይደለም’ ሲሉ የተናገሩት የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮና ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታዬ ደንዳዓ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

አቶ ታዬ ዛሬ ጠዋት አዲሱ ገብያ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ወደ ሥራ ቦታቸው ሲያቀኑ ነው በታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት የተወሰዱት።

የአቶ ታዬ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ አቶ ታዬ መታሰራቸውን እንጂ የት እንደሚገኙ እንደማያውቁ ገልጸዋል። አቶ ታዬ በቅርቡ ‘በሞያሌ ከተማ የተፈጸመው ግድያ በስህተት የሆነ አይደለም’ ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃን አስተያየታቸውን መስጠታቸው ይታወሳል። #MinilikSalsawi