የኮፕት ቤተ ክርስቲያን ለዴር ሡልጣን እድሳት በፈጠረችው ዕንቅፋት የእኅትማማች ግንኙነቱ እየተበላሸ ነው፤“ጸጸትና ርኅራኄ የላቸውም” /ፓትርያርኩ/

ገዳሙን ለማደስ የእስራኤል መንግሥት ቃል ቢገባም፣ኮፕቶቹ ዕንቅፋት ኾነዋል “ልቀቁና በራሳችን እናድሰው”ያሉትን፣መንግሥትም ቤተ ክርስቲያንም ተቃወሙ ፖፑ፥“ጠቅላላ ገዳሙ የእኛ ነው፤ መመለስ አለባችሁ፤”በማለት ለፓትርያርኩ ጻፉ ፓትርያርኩ፥“በእድሳቱ አያገባችሁም፤አንጡራሀብታችን ነው፤” ሲሉ መለሱላቸው “በውጭ ቢኾንም በኢትዮጵያ ቅርስነቱ መንግሥት ሊጠብቀው ይገባል፤”ሲሉ አሳሰቡ ኮፕቶቹ፥“መንግሥት በቤተክርስቲያን ላይ ግፊት ያድርግልን፤”ቢሉም