ፍልሚያ፦ ለወርቃማው በርጩማ

በ20ኛው ክፍለ ዘመን መንደርደሪያ ላይ ዛሬ ጋና ብለን በምንጠራት ምድር የብሪታንያ ቅኝ ገዢዎችን ተፋልመዋል፤ ያ ናና አሣንቴዋ። የእኚህ አፍሪቃዊት ኅልፈተ-ዜና ከተሰማ አንድ ምእተ-ዓመት ሊደፍን ጥቂት ቢቀረውም ያ አሣንቴዋ ዛሬም ድረስ በጋና እና በአፍሪቃ ልዩ በኾነ መልኩ እጅግ ብርቱ እና ጠንካራ