ላቲን የኦሮምኛን እድገት በእጅጉ ጎድቶታል – ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

የኦህዴድድ ከፍተኛ አመራር አባል የነበሩት፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያዉይና ብቻ ሳይሆን የጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነው፣ ብቃት ያለው፣ የግ እዝ ፊደል እያለ፣ የላቲን ፊደልን ለኦሮምኛ መጠቀም ትክክል እንዳልነበረ ገልጸው፣ ላቲን በአፋን ኦሮሞ እድገት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽኖ እንዳሳደረበትና ቋንቋዉን በተቀረው የኢትዮጵያ ማህበረሰብዝ እንድ እንዳያድግ መሰናክል እንደሆነ በመግለጽ አፋን ኦሮሞ በግ እዝ መጻፍ እንዲጀመር ጠየቀዋል።

በአማራ ክልል ኦሮሞኛ እንደ ትምህርት እንዲሰጥ በመጠየቀ ለአማራ ክል ፕሬዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሳፉት ደብዳቤ፣ የአማራ ክልል አፋን ኦሮሞን በግእዝ ፊደል በማስተማር ፈር ቀዳ እንዲሆንም ተማጽነዋል።

የፕሬዘዳንት ግርማ ደብዳቤ ከዚህ በታች አስፍረናል፡

ተከበሩ የአማራ ክልል መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ዉድ የተከበሩ አቶ ገዱ

“ንብ ቢያብር አንበሳን ያስር”  እንደሚባለው በሕብረትና በአንድነት የማይፈታ ችግር የማይታለፍ ድልድይ የለም። እኛ ኢትዮጵያዉይን ዘር ፣ ሃይማኖት ሳይከፋፈለን በአንድነት በመቆማችን ከኛ በላይ በዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁትን ጠላቶች ለመመከትኛ የአገራችንን ነጻነት ለማስጠበቅ ችለናል።

አሁን አገራችን የዉጭ ወራሪ ጠላቶች ባይኖሯትኝ እንደ ድህነት፣ በሽታ፣ የኋላ ቀርነት፣ መከፋፈል የመሳሰሉ ጠላቶች አሏት። አሁንም ሌሎች አገሮች ከደረሱበት አንጻር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ለዚህም ነው ኢትዮጵያዉያን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መያያዝ ያለብን። በርስ በርሳችን ያሉ መከፋፈሎችና አጥሮችን ማፍረስ አለብን።መግባባት መነጋገር፣ መቀራረብ መቻል አለብን። እነርሱና እኛ የሚለውን አቁመን ሁላችንም “እኛ” ማለት መጀመር አለብን።

ለዚህም ነው በአማራ ክልል አፋን ኦሮሞ እንደ ትምሀርት እንዲሰጥ የሚጠይቅ ጽሁፍ ምሁራን ለርስዎ እንደጻፉ ሳነብ ደስታ የተሰማኝ። አፋን ኦሮሞ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የሚናገሩት የኢትዮጵያዉያን ሁሉ የሆነ ቋንቋ ነው። ይህ ቋንቋ ከኦሮሚያ አልፎ በሌሎች ክልሎች እንደ ትምሀርት መሰጠቱ የበለጠ መግባባትን የመበለጠ መቀራረብን የሚያመጣ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል መደረግ የነበረበት ጉዳይ ነው። ሊደገፍ ብቻ ሳይሆን ለተግራዊነቱም የሁላችንንም ድርሻ የሚጠይቅ ነው።

አብዛኛው ኦሮምኛ የማይናገር ኢትዮጵያዊ አፋን ኦሮሞ የመማርና የማወቅ እድል ቢመቻችለት ለማወቅና ለመማር ትልቅ ፍላጎት የሚኖረው ነው የሚመስለኝ። የአማራ ክልል መስተዳደርም አፋን ኦሮሞ በክልሉ ማስተማር ቢጀምር የሕዝብ ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል ብዬ አስባለሁ።

ሆኖም ግን ሁሉንም የአገራችን ቋንቋዎች በትክክል ለመጻፍ ብቃት ያለው፣ የራሱ የኦሮሞ ማህበረሰብም የሆነ፣ በአፍሪካ ብቸኛ የጥቁር ሕዝብ ፊደል ተደርጎ የሚወሰድ፣ የሚያኮራ የግእዝ ፊደል እያለን፣ ላቲን ለኦሮምኛ መጠቀሙ ትክክል አልነበረም። የኦሮምኛን እድገት በእጅጉ ጎድቶታል። በሌላው ማሀብረሰብ ዘንድ ኦሮምኛን የመማር ፍላጎትን እንዳይኖር ሆኗል። ያለ ፍላጎት ደግሞ በግድ አስገድዶ ወይም በአዋጅ የሚሆን ነገር አይኖርም። ስለዚህ የአፋን ኦሮሞ ተቀባይነትም ለማሳደግ ሕዝብ በፍቅርና በፍላጎት እንዲማረው ለማበረታታ የአማራ ክልል መስተዳደር ግእዝን እንዲጠቀም በአጽንዎትና በአክብሮት እጠይቃለሁ።