የቀድሞ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በአማራ ክልል ኦሮሚኛ ቋንቋ በሳባ ፊደላት እንዲሰጥ ጠየቁ ።

የቀድሞ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የአማራ ተወላጆች የኦሮሚፋ ቋንቋን በሣባ ፊደላት እንዲማሩ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለክልሉ መስተዳድር መላካቸው ተሰማ፡፡

በአማራ ክልልና በሌሎች ቦታዎች የሚገኙ ሰዎች ጭምር የኦሮሚፋ ቋንቋን ከላቲን ፊደላት ይልቅ በሣባ ፊደላት ቢማሩ በቀላሉ ቋንቋውን መልመድ ይችላሉ ሲሉ ፕሬዝዳንት ግርማ ለሸገር ነግረዋል፡፡

አፋን ኦሮሞን ማወቅ የሚፈልጉ የአማራ ተወላጆች ቋንቋውን ማወቅ እንዲችሉ የክልሉ መንግስት በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ቢያስገባ በቀላሉ ማስተማር ይቻላል የሚሉት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ሀሳባቸውን ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ከረጅም አመታት በፊት መፅሐፍ ቅዱስ መፅሐፈ ቁልቁሉ በሚል በሣባ ፊደል መተርጎሙን የተናገሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት አሁንም ብዙ ድምፆች ያሉትን የላቲን ፊደላት ከማስተማር ይልቅ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን በሳባ ፊደላት መስጠት ቢቻል የቋንቋው ተናጋሪ ያልሆነውን ሰው በቀላሉ ማስተማር ይቻላል ብለዋል፡፡

የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በሣባ ፊደላት በአማራ ክልል ውስጥ በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ቢካተት መልካም ነው የሚለውን ሀሳብ ለክልሉ ርዕሠ መስተዳደር ጭምር ደብዳቤ መፃፋቸውን የቀድሞው ፕሬዘዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ነግረውናል፡፡

(የኔነህ ሲሳይ)