ቄሮ የተባለው ቡድን ደግሞ አድማውን ከቦቴ መኪኖች ወደ ባቡር ፉርጎዎች አዞራለሁ ብሏል።

መንግስት የነዳጅ አቅርቦት ችግር የለም ሲል ቄሮ የተባለው ቡድን ደግሞ አድማውን ከቦቴ መኪኖች ወደ ባቡር ፉርጎዎች አዞራለሁ ብሏል።

የነዳጅ አቅራቢ ድርጂቱ ሀገሪቱ በየቀኑ የሚያስፈልጋት የነዳጅ አቅርቦት ያለምንም ችግር እየቀረበ ነው በማለት መግለጫ ሰጥቷል።

ሀገሪቱ በየቀኑ የሚያስፈልጋት የነዳጅ አቅርቦት ያለምንም ችግር እየቀረበ ነው በማለት አድማው እንደማያሳስበው አስታውቋል።

ሀገሪቱ በየቀኑ የሚያስፈልጋት ነዳጅ 1.2 ሚሊዮን ሊትር ቢንዚን፣ ከ7-8 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ እንዲሁም 2.1 ሚሊዮን ሊትር ቢሆንም እስከ ዛሬ ድረስ የነዳጅ አቅርቦቱ ከፍላጎቱ በላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለማርያም ገልጸዋል ሲል የኢትዮጵያ ቴሌቪዢን ዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ ላለፉት ሶስት ቀናት በሀገሪቱ ውስጥ ምንም አይነት ነዳጅ ጫኝ ቦቴ መኪኖች እንዳይዟዟሩ አድማ ሲጠራ የቆየው “ቄር” የተባለው ቡድን አሁን ፊቱን ወደ ባቡር ፉርጎዎች እንደሚያዞር ገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ ለአንድ ሳምንት ብቻ ተጠርቶ የነበረው የነዳጅ ማቀብ አድማው ምናልባትም ሊራዘም እንደሚችል ነው የተነገረው።

ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ መንግስት ባቡርን ጨምሮ በሌሎች መንገዶች ነዳጅ ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ ሊያስገባ እንደሚችል ፍንጮች በመውጣታቸው ነው ብሏል።