ወያኔ በሱስ ያደነዘዘው ትውልድ

ወያኔ በሱስ ያደነዘዘው ትውልድ

የሸገር ራዲዮ ዘገባ እንዲህ ይላል…..

“እድሜያቸው ከ10 እስከ 24 ዓመት ከሚሆናቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች 51 % ያህሉ ጫት ቃሚዎች ናቸው – 45.6 %ቱ ደግሞ የአልኮል መጠጥ ይጠጣሉ – ጥናት…

ኢትዮጵያ ወጣቶችዋ በሱስ፣ በጤና እክል፣ በሥነ ልቦናዊ እና የሥነ ተዋልዶ ችግሮች ተተብትበዋል፡፡ ጫት፣ ሺሻ፣ የአልኮል መጠጦች እና ማሪዋናን የሚወስዱ ወጣቶች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው፡፡

ከኢትዮጵያውያን ወጣቶች 45.6 ከመቶዎቹ የአልኮል መጠጥ ይጠጣሉ፤ 51 ከመቶዎቹ ደግሞ ጫት ቃሚ ሆነዋል:: ከቃሚዎቹ መካከል 56.6 ከመቶዎቹ ወንዶች ናቸው፡፡

ከሱሱም በተጨማሪ ኤች አይ ቪ፣ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና ራስን ማጥፋት የበርካታ ወጣቶችን ሕይወት የሚቀጥፉ ሰበቦች ናቸው ተብሏል፡፡”

ሃይለማርያም ደሳለኝ ከ2 አመታት በፊት ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሙህራን ጋር ውይይት ሲያደርግ የተነሳው አንዱ ጉዳይ “ወጣቱ በሱስ ነተበ: ጫት መቃም በጣም ተስፋፋ” የሚል ጉዳይ ነበር:: ሃይለማርያም ግን ከማሾፍ የማይተናነስ መልስ ነበር የመለሰ…”የጫትን ጉዳት አጥንታቹህ አሳዩንና ርምጃ እንወስዳለን…..”

ጫት ግለሰብን: ቤተሰብን: ሃገርን እንደሚጎዳ ሳያውቅ/ሳያምን ስልጣን ላይ ቂብ ብሎ የኖረ መሪ::
ወጣቱን አደንዝዞና ተስፋ አስቆርጦ ሃገር መዝረፍ የወያኔ ተልዕኮ ነው:: ጠያቂ ያልሆነ ነፈዝ ትውልድ እንዲኖር ይፈለጋል:: የወጣቱ ዛሬውም ነገውም ጨልሟል:: ሃገሪቱ ተረካቢ ትውልድ እያጣች ነው::