በታች አርማጭሆ በገበሬው ላይ ጦርነት የከፈቱ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል

በታች አርማጭሆ በገበሬው ላይ ጦርነት የከፈቱ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፤

Muluken Tesfaw

ዛሬ መጋቢት 07 ቀን 2010 ዓም ከረፋዱ 4.00 ሰዐት አካባቢ ብዛት ያለው የአገዛዙ ሠራዊት ትጥቅ ለማስፈታት በሚል ወደ ታች አርማጭሆ ሙሴባንብና ጅንግር አካባቢ ተንቀሳቅሶ ነበር፡፡ አስቀድሞ በጅምላ ከገበሬዎች ቤትና ንብረት ላይ ተኩስ የከፈተው የአገዛዙ ሠራዊት ገበሬው ራሱን ለመከላከል በወሰደው እርምጃ ወደቀጠናው የገቡ ወታደሮች በሙሉ ተደምስሰዋል፡፡

ከሰዐት በኋላ ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው ገብቶ የሳንጃ፣ የአሽሬና ሙሴ ባንብ አካባቢ የጦርነት ቀጠና እንደሆነ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያሳየው፡፡