ሞያሌ የተፈፀመዉ ግድያ እና የለንደኑ ተቃዉሞ

ባለፈው ሣምንት ቅዳሜ በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ የመከላከያ ሠራዊት በነዋሪዎች ላይ የፈጸመው ግድያ በየአቅጣጫው ቁጣን ቀስቅሷል። የኮማንድ ፖስቱ ድርጊቱ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የተከሰተ መሆኑን ቢገልፅም የመከላከያ ኃይሉ ጥቃት ሆን ተብሎ የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት እንደኾነ የገለጡ አሉ።