አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያምና የቀጠለው እስራት፣ ግድያ

ባለፍነው ቅዳሜ ሞያሌ ከተማ ውስጥ የመከላከያ ሠራዊት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈጸመውን የግድያ ጥቃት በተመለከተ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በርካታ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።  ከግድያው ባሻገር ሰዎች ለስደት እና ለእስር መዳረጋቸውም አነጋጋሪ ኾኗል። ለታዋቂው የጥበብ ሰው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ሕክምና ትብብር መጠየቁም ሌላዉ ጉዳይ