የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፅ/ቤት የምስረታ ውይይት ተደረገ::

ዛሬ መጋቢት 8/2010 ዓ/ም የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፅ/ቤት የምስረታ ውይይት ተደረገ::

በውይይቱ የንቅናቄው መሰረታዊ ሀሳቦችና እምነቶች በኢ/ር ይልቃል ጌትነት በውይይቱ ለተገኙ ኢትዬጵያውያን ተብራርቷል:: ኢ/ር ይልቃል የንቃናቄው መመስረት ያስፈለገው ፓርቲ መስርቶ ሌሎች ፓርቲዎችን ለመወዳደር ሳይሆን ከአገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ ለምናደርገው ትግል ኢትዮጵያውያንን ያካተተ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ለመፍጠር ነው ብለዋል::

የውይይቱ ተሳታፊዎችም የሚመሰረተው የስነ መንግስት ማህበር ሁሉን አቀፍ የሆነና ከዚህ በፊት ከነበሩብን ችግሮች ልምድ ወስደን የተሻለ ድርጅት እንዲፈጠር ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል::
የምስረታ ጉባኤው በተለየ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር በ15 ቀናት ውስጥ እንደሚደረግም የምስረታ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ስለሺ ፈይሳ ተናግረዋል::