ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተባለ

የዓለም የምግብ መርኃ-ግብር ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ዜጎች “በኢትዮጵያ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምክንያት ምናልባት ቁጥራቸው ሊጨምር ይችላል” ሲል ሥጋቱን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፦ “የተፈናቀሉ እና ወደ ኬንያ ድንበር የሔዱ ዜጎቻችንን ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ” ነው ብሏል።