አባ ማትያስና ጎይቶም የዐማራና የኦሮሞ ካህናትን ከአዲስ አበባ እያጸዱ ነው

ትግራዋዮቹ አባ ማትያስና ጎይቶም
ብዙ የዐማራና ጥቂት የኦሮሞ ካህናትን
ከአዲስ አበባ እያጸዱ ነው ተባለ ።
*★★★*

ዳኛውም ዝንጀሮ መፋረጃው ገደል ፣
እምን ላይ ተቁሞ ይነገራል በደል ። አለ የሀገሬ ሰው ።

~ ጉቦ አልሰጥ ያሉ ጥቂት ትግሬዎችም ለዐመል ታህል ጠብ ተደርገዋልም ተብሏል ።

~ አባራሪዎቹ የመንግሥትን ፖሊሲ እያስፈጸሙ ስለሆነ ምንም ቅሽሽ ፣ ደንገጥም አያደርጋቸውምም ተብሏል ።

~ መምህር ባሕሩና ዳዊት ያሬድ በጉቦው ገንዘብ መሬትና ቡናቤት ከፍተዋልም ተብሏል ።

~ በምንፍቅናው ከቅዱስ ዮሴፍ የተባረረው ነሁሰናይ ደረጃውን ከፍ አድርገው ሳሪስ ሥላሴ በዋና ጸሐፊነት እንደመደቡትም ተሰምቷል ። ጉድበል ጎንደር ማለት አሁን ነው ።

#ETHIOPIA | ~ አዲስ አበባ ~ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ።

~ የትግራይ ተወላጆቹ ፓትሪያርክ አባ ማትያስና ዋና ሥራ አስኪያጃቸው አይተ ጎይቶም በአዲስ አበባ ሀገረስብከት ውስጥ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ያገለግሉ የነበሩ ከ150 በላይ የዐማራና የኦሮሞ ተወላጅ ካህናትን በዘመቻ መልክ ከሥራ ማባረራቸው ተነገረ ። ድርጊቱ በአዲስ አበባ ምእመናን ዘንድ ቁጣ ቀስቅሷል ። ከተባረሩት ካህናት መሃል በምንፍቅና የሚጠረጠሩም አብረው መኖራቸው ታውቋል።

~ በአሁኑ ጊዜ የተጠና በሚመስል መልኩ ትግርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችንን ገንዘብና ሀብት በሚገኝባቸው ቦታዎች ሁሉ የማስቀመጥ እና በኢኮኖሚ እንዲጠነክሩ የማድረጉ ተግባር እጅግ አይን ያወጣና ያፈጠጠ ነውረኛ ተግባር መሆኑ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ጣጣ እያመጣ መሆኑ እየተነገረ ነው ።

~ በመንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች የሚታየው የትግርኛ ተናጋሪዎች ሁሉን ነገር የመቆጣጠር አባዜ ወደ ቤተክህነቱ ዘው ብሎ የገባው ህወሓት አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ማግስት እንደሆነ ቢታወቅም በአሁኑ ሰዓት ግን በአባ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና እጅግ በሚቀፍ ሁኔታ ያለ ይሉኝታ ከላይ እስከታች ቤተክርስቲያኒቷ መቐለ መስላለች ይላሉ ታዛቢዎች ።

~ ዐማራውና ኦሮሞው አስራቱን ፣ ሙዳየ ምጽዋቱን ፣ ስእለቱን ለቤተክርስቲያን ይሰጣል ። ገንዘቡን ግን የሚጠቀሙበት እነ ጎይቶም ናቸው ። በጎይቶም ዙሪያ የተኮለኮሉት ኦሮሞው ዳዊትና የህግ ክፍሉ ባህሩ የጎይቶም አቀባባይ በመሆን ከፍተኛ ዘረፋ በመፈጸም ላይ መሆናቸውም ተነግሯል። አጅሬ ዳዊት ያሬድ ቡናቤት የከፈተ ሲሆን ፤ ባህሩ ደግሞ ወደ ሰንዳፋ በ 1 ሚልየን ብር አካባቢ የቤት መስሪያ መሬት ገዝቶ ይምነሸነሻልም ተብሏል ።

~ ፓትሪያርኩም ለማን እንደሆነ ወደ ፊት ይፋ በማወጣው ሰው ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ለሚያሠሩት ለግል ህንጻቸው ከእነ ጎይቶም በሚፈስላቸው ፈሰስ አፋቸው በመለጎሙ አንዳች ነገር ላለመናገር መሃላ ገብተዋልም ነው የሚባለው። እንዲያውም “ሙስና ቀላል ነገር መስሎኝ ነበር፤ በየዋህነት ነው፤ ምናልባት ቀጣዩ ትውልድ ይቀርፈው ይኾናል፤” በማለት በእሳቸው ጊዜ በእሳቸው ዘመነ ፕትርክና ሙስና እንደነገሠ መቀመጥ አለበት አትነካኩት በማለት በቴሌቭዥን ቀርበው መግለጫ እስከመስጠትም ደርሰዋል።

~ በጉዳዩ ላይ መፍትሔ ይኖረው እንደሆን ብለው የተባረሩት የዐማራና የኦሮሞ ነገድ አባላት ወደ ፌኩ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተብዬው ትግራዋዩ ዶር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ጋር በመሔድ ማነጋገራቸውም በትላንትናው ዕለት በወጣው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ተነግሯል ። አመልካቾቹ ቢጨንቃቸው እንጂ የትም ቢሔዱ መፍትሔ እንደማያገኙ የታወቀ ነው ። ምክንያቱም የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተብዬው ዋና ሐላፊ እኮ በትግራይ ዘረኝነት ያበደውና በምርጫ ቦርድ ሓላፊነት ዘመኑ ህወሓት 100% ፓርላማውን እንድትቆጣጠር ያደረገ ጀግና ነው ። እዚህ ሰው ጋት ሔደው ነው ተበዳዮቹ አቤቶታቸውን ያቀረቡት ።

~ የተበዳዮቹን የዐማራና የኦሮሞ ነገድ አባላት የሆኑ ካህናትን አቤቱታ ለይስሙላም ቢሆን ያዳመጡት ትግራዋዩ ዶር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር “አገሪቱ ጭንቀት ላይ እያለች፣ መጸለይ እንጂ መጉላላት አይገባችሁም፤” ነበር በማለት የአዛኝ ቅቤ አንጓች የምፀት ሀዜኔታቸውን አሳይተዋቸዋልም ተብሏል ።

~ ዶክተር አዲሱ አቤቱታ አቅራቢዎቹን ከማናገራቸው በፊት ለ4 ሰዓታት ያህል ማፍያውን ከእነ ጎይቶም ፣ ዳዊት ያሬድና መ/ር ባህሩ ጋ ሲመክሩ መቆየታቸውም ታውቋል ። በመጨረሻም አቶ አዲሱ ለተፈናቃዮቹ ዐማሮችና ኦሮሞ ካህናት ” እባካችሁ ለአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅና ቡድኑ “ለአንዴ ዕድል ይሰጠውና መፍትሔ ያብጅ” በማለት እቅጩን መናገራቸው ታውቋል ።

ዳኛውም ዝንጀሮ መፋረጃው ገደል ፣
እምን ላይ ተቁሞ ይነገራል በደል ። አለ የሀገሬ ሰው ።

የሚገርመው ነገር “ለዘመናት ያገለገሉ ካህናትና ሠራተኞች በጠራራ ፀሐይ ይሸጣሉ፤ይለወጣሉ፤” ብለዋል 250ዎቹ አቤቱታ አቅራቢ ተበዳዮች ። አንድ ለእረፍት አስፈቅዶ የወጣ ካህን እረፍቱን ጨርሶ ወደ ሥራ ገበታው ሲመለስ ሞተሃል ተብሎ ከሀገረ ስብከቱ ሌላ ሰው በአንተ ቦታ ተቀጥሯል እናም በቃ ሞተሃል እንደተባለም ታውቋል ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በበላይነት የሚመሩት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ አምስተኛ በዓለ ሢመታቸውን ምክንያት በማድረግ በቅርቡ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ የሙስና ጉዳይ አንስቶባቸው ቅዱስነታቸው እስኪ የሚሉትን እንስማ በሳቅ ፍርፍር እንብላ።

ኢኦተቤ ቴቪ፡- ቅዱስ አባታችን፣ የዛሬ አምስት ዓመት ጀምሮ የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት በአግባቡ እንዲጠበቅ፣ ሙስና እና ዘረኝነት ከቤተ ክርስቲያን እንዲጠፋ ለመጀመሪያ ጊዜ በዐደባባይ በዐዋጅ ያወገዙት ቅዱስነትዎ እንደኾነ ይታወቃል፡፡ አሁንስ በዚህ ዙሪያ ሙስና እንዲወገድ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ምን መደረግ አለበት? አንዳንድ ጊዜ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም አህጉረ ስብከት በጎ ተግባራት እንዳሉ ኹሉ አቤቱታ የሚያሰሙ ምእመናን ሲመጡ ይስተዋላል፡፡ ቅዱስነትዎ፣ አሁንም የእርስዎ መመሪያ ስለሚያስፈልግ በዚህ አጋጣሚ ቢገልጹልን፤

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፡- እኔ በእውነቱ ያው እንዳሉት ኹሉ ከመጀመሪያ ጀምሮ ስለ ሙስና ብዙ ተናግሬአለሁ፡፡ ሰው ግን ያው በደንብ ነገሩን ኹሉ የተመሰቃቀለ መኾኑን ስለሚያውቅ፣ ያው እኔ በየዋህነት ነው ከመጀመሪያው ጀምሮ ቀላል ነገር መስሎኝ ነበር፤ ግን ቀላል ነገር እንዳይደለ ነው የተረዳኹት፤ ለምን፣ በኔትወርክ የተያያዘና የተሳሰረ በመኾኑ፣ እንደ ሸረሪት ድር ያደራ በመኾኑ እስከ አኹን ምንም ሊደረግ አልቻለም፡፡

ብዙ ተደርጓል በርግጥ፤ ብዙ ተሻሽሏል፤ ለምሳሌ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሙዳየ ምጽዋቱ ገንዘብ በባንክ ሠራተኞች እንዲቆጠርና በትክክል ወደ ባንክ እንዲገባ እየተደረገ ነው ያለው፤ ከዚያም የተነሣ መቸም በቅርቡ የምናየው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ነው፤ የፐርሰንቱ ዓመታዊ ገቢ ካለፉት ዓመታት ከድሮው እየተሻሻለ መጥቷል፡፡

ነገር ግን ችግሩ የቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይኾን የሀገሩ ጣጣ፣ የሀገሩ ችግር ነው፡፡ ሙስና በየትም ዓለም ያለ ነው፤ የአፍሪቃ መሪዎች ተሰብስበው ትልቁ አጀንዳ እርሱ ነበር፡፡ ሙስና(corruption) እየተባለ ትልቅ አጀንዳ ነበር፡፡ ገንዘባችንን በትክክል ብንሰበስብ ከፈረንጆች ልመና፣ ስጦታ ወይም ብድር እንድን ነበር፤ ገንዘባችን እየተመዘበረ ነው ያለው ብለው በየዓመቱ ይህን ያህል በቢሊዮን የሚቆጠር እንከስራለን ብለው በዚህ ነው የዋሉት፤ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ሙስና፥ ሥር የሰደደ መጥፎ፣ መጥፎ ነገር ነው ያለው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለረብሻውም መነሻ የሚኾነው እርሱ ነው፡፡ “ሙስና በዝቷል፤ አገር ተጎድቷል፤” እየተባለ ነው መነሻ እየኾነ ያለው፡፡”

ሰው ምናለ ያልተሰጠውን ከመውሰድ የተሰጠውን በሥነ ሥርዐት ቢመገብ፣ ቢበላ፤ ሥርዐት ያለው ደመወዝ እያገኘ እንደገና ደግሞ በአጭር ጊዜ ለመበልጸግና ያልታዘዘልንን ሀብት ለመብላት… በእውነቱ ይህን እንዲጠነቀቅበት ነው፡፡ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ምን እናድርግ ብለው የንሥሓ ጥምቀት ለመጠመቅ የሔዱ ሰዎች፣ በሕግ የተሰጣችሁ ደመወዛችሁ ይብቃችሁ ነበር፤ ያላቸው፡፡ ያልተሰጣችሁን ሰውን አትበዝብዙ፤ ሰውን አትጉዱ፤ ሕግ ያዘዘላችሁን ነገር ተመገቡ፡፡

እና ይኼ ሀገርን የጎዳ፣ ወገንን የጎዳ መቼም ያልታወቀ ጉዳት በሀገርና በወገን ላይ እየተካሔደ ያለው ነው፡፡ ይኼን ጸያፍ የኾነ ነገር ቤተ ክርስቲያን በደንብ ነው የምታወግዘው፡፡ በየጊዜው እናስተምርበታለን… ግን ያው በመጠኑ ትንሽ ትንሽ ለውጥ ቢታይም ችግሩ አለ፤ ችግሩ ግን እስከ አሁን ድረስም አለ፤ ወደፊት ምናልባት ትውልዱ ይቀርፈው ይኾናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን በማለት እኛ ትግርኛ ተናጋሪዎች በሥልጣን ላይ እስካለን ድረስ በዘረፋ ጉዳይ ጠያቂም ተጠያቂም የለም በማለት ነጭ ነጩን ነግረውን ዕርፍ ብለዋል ። አከተመ ።

~ አሁን ባለው ሁኔታ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት 90% ትግራዋይ ናቸው ። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ጨምሮ የጠቅላይ ቤተክህነቱ የመምሪያ ሓላፊነት ቦታዎች በሙሉ በትግራዋዮች ነው የተያዘው ፣ የገቢ ምንጫቸው ከፍ ያሉት የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት በሙሉ ከእልቅና እስከ ጽዳት የተያዙት በትግራዋዮች ነው ። ይኽም አላንስ ብሎ ግድየለም ጊዜ ያመጣውን ጊዜ ይመልሰዋል በሚል የእግዚአብሔርን መልስ በመጠባበቅ ላይ ያሉ የዐማራና የኦሮሞ ነገድ አባላትን ከሥራ ገበታ በማፈናቀል በረሃብ እንዲያልቁ ማድረግ እንደምን ያለ የጭካኔ ተግባር ነው ሲሉ ብዙዎች ይጠይቃሉ ።

~ ካህናቱ ለአቤቱታ ፖሊስ ጣቢያ ሲሔዱ የሚያገኛቸው ትግሬ ነው ። ቤተክህነት ያባረራቸው ትግሬ ነው ። ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ቢሔዱ ወዲ ገብረ እግዚአብሔር ነው ። የጨነቀ ነገር ሆነ እኮ ይላሉ የአቤቱታ አቅራቢዎቹን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉ ታዛቢዎች ። በነገራችን ላይ እነ አይተ ጎይቶም ጉቦ ጠይቀዋቸው አልሰጥ ያሉ ሁለት የትግራይ ብሔር ተወላጆችንም ማባረራቸው ተገልጿል ። ተባራሪዎቹ ጀርባቸው ሲጠና አያታቸው ዐማራ ሆነው ተገኝተው ይሆንን.?

~ በቤተክርስቲያኒቱም ሆነ በሀገሪቱ ሪሶርስ እንዴት አንድ ብሔር ብቻ በስግብግብነት ይጠቀማል.? ነገሩ በኋላ ችግር አያመጣም ወይ.? የእኔ ጥያቄ ነው ።

#ማስታወሻ ፦ ዛሬና ትናንት በቂሊንጦ ጀሚገኙትን አባቶች ለመጠየቅ የሔደው የህዝብ ቁጥር አስደማሚ ነው ተብሏል። በተለይ የእስልምና እምነት ተከታዮች በቤተሰብ ደረጃ በግሩፕ ሔደው አባቶችን መጠየቃቸው አስደናቂ ሆኖ ተገኝቷል ። የማኅበረ ቅዱሳን አባላትም ምክራችንን ሰምተው በማረሚያ ቤቱ ተገኝተው አባቶቻችንን ሲያጽናኑ ተስተውለዋልም ተብሏል ። እናም ነገም በልደታ ፍርድ ቤት በ4ተኛ ወንጀል ችሎት አባቶቻችን ቀጠሮ ስላላቸው ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ የቻላችሁ በቦታው ተገኝታችሁ ችሎቱን በመከታተል መረጃ ታደርሱን ዘንድ እናመለክታለን ።

ሻሎም.! ሰላም.!

አመልካች ፦

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
መጋቢት 9/2010 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ