ሹመት በኢሕአዴግ ቤት ስምሪት ነው ፤ ኢሕአዴግ የምሾመው ጠቅላይ ሚኒስትር የፓርቲውን ፕሮግራምና ውሳኔዎች የሚፈፅም እንጂ በራሱ የሚወስን አይደለም ብሏል

#Ethiopia : ኢሕአዴግ የምሾመው ጠቅላይ ሚኒስትር የፓርቲውን ፕሮግራምና ውሳኔዎች የሚፈፅም እንጂ በራሱ የሚወስን አይደለም ብሏል ፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከባለፈው የተለየ የሚሰራው ስራ የለም ድርጅቱ ስምሪት እንጂ ወሳኝ ስልጣን አይሠጥም ተብሏል ፤ ኢሕአዴግ ያለውን ያንብቡ ።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ኢህአዴግ ነው! በምርጫ አሸንፎ ይህችን ሃገር የመምራት ሃላፊነት የተረከበው ኢህአዴግ ነው፡፡ ተወዳድሮ ያሸነፈው የኢህአዴግ ፕሮግራም ነው፡፡ ስለሆነም ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚሆነውም ኢህአዴግ ነው፡፡ ሰው በሰው ሊተካ ይችላል፡፡ ተተክቷልም! የሚቀጥለው ግን መስመሩና የድርጅቱ ፖሊሲና ስትራቴጂ ነው፡፡ ለውጥ የሚያመጣውም ግለሰብ ሳይሆን የጠራውና በተግባር ተፈትኖ ውጤታማነቱ የተረጋገጠው የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመር ብቻ ነው! ስለዚህም ነው ለኢህአዴጎች የጠቅላይ ሚኒስቴር ምርጫ ትልቅ አጀንዳቸው ሊሆን የማይችለው፡፡ በኢህአዴግ ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት የስምሪት ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ፕሮግራም ፤ከሁሉም በላይ መስመር፤ ከሁሉም በላይ ውድ ዋጋ የተከፈለበት የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመር፡፡ ከኢህአዴግ የተለየ ፕሮግራም የሚፈፅም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊመጣ የሚችለው ከኢህአዴግ ውጪ ብቻ ነው!

ኢሕአዴግ ለለውጥ ያልተዘጋጀ ፓርቲ መሆኑን በተደጋጋሚ እያሳየ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ መምጣት የሚችለው በሕዝብ ትግል እንጂ የኢሕአዴግን ሹመት በማጀብ አይደለም ። #MinilikSalsawi