የዋልድባ መነኮሳት ጉዳይ የፍርድ ቤት ውሎ

የዋልድባ መነኮሳት ጉዳይ!

በሽብርተኝነት ተከስሰው ከ2009 ዓ ም መጀመሪያ ወራት ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙት ሁለቱ የዋልድባ መነኮሳት አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም እና አባ ገ/ሥላሴ ወ/ሃይማኖት ዛሬ መጋቢት 10/2010 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።


መነኮሳቱ ለዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት በእስር ቤት አስተዳደር የምንኩስና ልብሳቸውን አውልቁ መባላቸውንና ሌሎች ሰብዓዊ መብቶቻቸው እየተጣሱ መሆኑን በመግለፅ ላቀረቡት አቤቱታ ብይን ለመስማት ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ አቤቱታዎቹን በመቀበል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ብይን ከመስጠቱ በፊት ተከሳሾች ልብስ እንዲቀይሩ የሚለውና እና የዞን ቅያሬ ቅሬታው በእስር ቤቱ አስተዳደር መፈታቱን በጠበቃቸው በኩል ገልፀዋል።
በተከሳሾች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ለመጋቢት 18/2010 የተያዘው ቀጠሮ እንደተጠበቀ ነው።
የዛሬውን ችሎት ለመነኮሳቱ አጋርነት በማሳየት በርካታ ሰዎች ታድመውታል። ችሎቱን የመሩት የከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ምክት ፕሬዚደንት አቶ በሪሁ ተክለብርሃን ናቸው።