የገበሬውን ትጥቅ ለማስፈታት የዘመቱ የኢሕአዴግ ወታደሮች በጀግኖቹ ተገድለዋል።

በአርማጭሆ የገበሬውን ትጥቅ ለማስፈታት የሄዱ 17 ያክል ወታደሮች ተገድለዋል፤

Muluken Tesfaw : በላይና ታች አርማጭሆ ወረዳዎች የአገዛዙ ጦር ትጥቅ ገበሬውን ለማስፈታት ከሰሞኑ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ገበሬው ባልሞት ባይ ተጋዳይነት ባደረገው ርብርብ በሁለት ቀናት ብቻ ከ17 በላይ ወታደሮች ተገድለዋል፡፡ የዐማራ ገበሬዎች አርሰን መብላት ባለመቻላችን እንድንሸፍት ተገደናል ብለዋል፡፡ ከሮቢት አካባቢ ያነጋገርናቸው ሰዎች እንደሚሉት ‹‹ወታደር ድንበር ሲጠብቅ ነበር የምናውቀው፤ የእኛ አገር ግን አርሰን እንኳን እንዳንበላ ከልክሎናል ድንበራችንን ግን ሱዳን እንደፈለገ ይፈነጭበታል›› ሲሉ አስተያታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በአስቸኳይ ይህ ሁኔታ ካልተስተካከለ የሚጠፋው የሰው ሕይወት ከመጨመሩም በላይ የበለጠ ትርምስ ሊፈጥር እንደሚችል ስማቸው እንዳይጠቀስ የሚፈልጉ የወረዳ ባለሥልጣናትም ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ አገዛዙ የሃይማኖት አባቶችን በሽምግልና በግዴታም እየላከ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡