ኤርትራ በኢህአዴግ የቀረበባትን ክስ አጣጣለች

ኤርትራ በኢህአዴግ የቀረበባትን ክስ አጣጣለች (ኢሳት ዜና ማጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ኤርትራ ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ እያደረገች ነው በማለት በህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ በኩል የቀረበውን ክስ፣ ኤርትራ አጣጥላዋለች። “ኢትዮጵያ ችግሩን ውጫዊ ለማድረግ ከመፈልግ ይልቅ፣ እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ተቃውሞውና አለመረጋጋት ለመፍታት ብትሰራ ይሻላታል”