ትግራይ ባሉ ዩንቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ገንዘብ ማስላክ ችግር ሆኖብናል ብለዋል

ትግራይ ባሉ ዩንቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ገንዘብ ማስላክ ችግር ሆኖብናል ብለዋል፤ Mulukem Tesfaw

ከአክሱም፣ አዲግራትና መቀሌ ዩንቨርሲቲዎች የሚማሩ የዐማራ ተወላጆች ከቤተሰብና ውጭ ከሚኖሩ ዘመዶቻቸው የሚላክ ትንሽ ገንዘብ ለማውጣት በባንክ ሠራተኞችና በደኅንነቶች እንደተቸገሩ ገልጸዋል፡፡

በመጀመሪያ ከአክሱም ዩንቨርሲቲ የሚማሩ ልጆች በገለጹልን መሠረት ባንክ ቤቶች ሲሔዱ የመጡበትን ቀበሌ የሚያሳይ መታወቂያ (ከዩንቨርሲቲው በተጨማሪ) እንደሚጠየቁና ዐማራ መሆናቸው ሲጠረጠር (ሲታወቅ) ገንዘቡን ለምን እንዳስላኩት አሳማኝ የሚባል ማስረጃ ካላቀረቡ ብዙ እንደሚጉላሉ ገልጸዋል፡፡ በተለይ የተላከው ገንዘብ ከ500 ብር ከበለጠ ጥያቄው እና ማጉላላቱ የበዛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከአክሱም ዩንቨርሲቲ የሚማሩ ልጆች እንደነገሩን ገንዘብ እንዳያወጡ የታገዱ ልጆች ሁሉ አሉ ብለውናል፡፡