በአርማጭሆ ከመሣሪያ ገፈፋ ጋር በተያያዘ መነኮሳትና የቤተ ክርስቲያን አባቶች ተገድለዋል

በአርማጭሆ ከመሣሪያ ገፈፋ ጋር በተያያዘ መነኮሳትና የቤተ ክርስቲያን አባቶች ተገድለዋል፤ Muluken Tesfaw

በአርማጭሆ ሮቢት አካባቢ መሣሪያ ለመንጠቅ የገባው የአገዛዙ ጦር በጅምላ ሕዝቡ ላይ ጦርነት ከፍቷል፡፡ በዚህ ሳምንት ብቻ በርካቶች መሣሪያችሁን አስረክቡ ሲባሉ ባልሞት ባይ ተጋዳይነት የአገዛዙን ጦር እየገደሉ ተሰውተዋል፡፡ ”
ብራና ራዲዮ

የጣና ማኅበረ ሥላሴ ገዳም መነኩሴ የነበሩት አባ ደስታው ገነቱ በጅምላ ጦርነት የታወጀባቸውን ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ወደ እንጭቆ አርማጭሆ በሔዱበት ወቅት ቤተሰባቸው ላይ ጦርነት ይከፈታል፡፡ በዚህ ወቅት አባ ገነቱ ቀያችን ለቀን ከምንሔድ በጦርነት ብንዋደቅ ይሻላል በሚል ሁለት የአገዛዙ ወታደሮችን ገድለው አንድ ደግሞ አቁስለው በክብር ተሰውተዋል፡፡ አባ ደስታው ዛሬ ቀብራቸው መፈጸሙን ሰምተናል፡፡