የታሰሩት አባቶች ልብሰ ምንኵስናቸው ከመልበስ እንዳይከለከሉ ፍ/ቤት አዘዘ፤ “ክሡ የማይቋረጥበት ሕጋዊ ምክንያት አይታየኝም”/ጠበቃው/

ምስክሮችን ለማቅረብ ዳተኝነት የታየበት ዐቃቤ ሕግ፣ በቂ ምክንያት ከሌለ በስተቀር ምስክሮቹን በዕለቱ እንዲያቀርብ ፍ/ቤቱ አስጠነቀቀ አባ ገብረ ኢየሱስ ከ“ቅጣት ቤት” ወጥተዋል፤ ኹለቱም በዞን አንድ ይገኛሉ፤ አጠቃላይ ኹኔታው የተሻሻለ መኾኑን ገልጸዋል፤ ††† (የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ፤ መለስካቸው አምኃ፤ መጋቢት 10 ቀን 2010