ለጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ዓይኖች በእነዚህ ሰዎች ላይ ናቸው

የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ማዕከላዊ ስብሰባ ተጠናቆ ወደ ምክር ቤት ስብሰባ ተሻግሯል። 180 አባላት ያሉት ምክር ቤት ከሚወያይባቸው አበይት አጀንዳዎች አንዱ የፓርቲውን ሊቀ-መንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያምን የሚተካ መሪ መምረጥ ነው።