በወሎ ክፍለሐገር የተለያዩ ከተሞች ላይ ተነስቶ ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ብዙዎች አሁንም በእስር ላይ ናቸው

በአማራ ክልል ወሎ የተለያዩ ከተሞች ላይ ተነስቶ ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ብዙዎች አሁንም በእስር ላይ ናቸው
* ከታሰሩት መካከል የ8 ወር ነፍሰጡር ትገኝበታለች

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ወልዲያ ከተማ የጥምቀት በዓል ላይ ተነስቶ ወደተለያዩ የአካባቢው ከተሞች ተስፋፍቶ ሲካሄድ ከነበረውና ብዙዎች ህይወታቸውን ካጡበት የህዝብ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ብዙዎች አሁንም ድረስ በተለያዩ እስር ቤቶች እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። ከእስረኞች መካከል የ8 ወር ነፍሰጡር ትገኝበታለች።
እስረኞቹ ከወልዲያ፣ መርሳ፣ ቆቦ፣ ሮቢትና አካባቢው ታፍሰው የታሰሩ ሲሆን፣ ፍርድ ቤት ቀርበው ዋስትና ቢጠይቁም ዋስ መብታቸው ተነፍጎ በእስር ላይ ናቸው። ከመርሳ ከተማ የታሰሩ በርካቶች ዛሬ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወልዲያ ምድብ ቀርበው ነበር። እስረኞቹ በህዝባዊ ተቃውሞው ወቅት “ወያኔ ሌባ፣ በወያኔ አንገዛም በማለት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ንግግሮች አድርገዋል” የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ተገልፁዋል።
ከእስረኞቹ መካከል መርሳ ከተማ ላይ የታሰሩና በአንድ መዝገብ የተካተቱት የሚከተሉት ናቸው።
1, ኃይሉ አስፋው
2, ጌታቸው አባይ
3, ደምሴ ክብረት
4, አያሌው ፀጋዬ
5, ሰማው መንገሻ
6, ወርቅነሽ መንገሻ (የ5ኛ ተከሳሽ እህት)
7, ንጋቱ አየነው
8, ተስፋዬ ካሳዬ
9, ቢኒያም አለሙ
10, ሰይድ አያሌው
11, ኤፍሬም፣ …. ናቸው።

በሌሎች ከተሞችም ሆነ በመርሳ ያለው የታሳሪዎች ቁጥር በርካታ መሆኑ ታውቋል።