ኢትዮጵያዊው ቶማስ ኤድሰን ግርማ ዘለቀ አረፉ!

ኢትዮጵያዊው ቶማስ ኤድሰን ግርማ ዘለቀ አረፉ!

አቶ ግርማ ዘለቀ ትውልዳቸው ባሕር ዳር ሲሆን በሕይወት ዘመናቸው ከ ቀ.ኃ.ሥ ዘመን ጀምሮ በርካታ የፈጠራ ሥራዎችን ያበረከቱ ሰው ነበሩ። ከነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

1. ሰዓቱን እየጠበቀ የሚደውል የትምህርት ቤት ደውል (በቀ.ኃ.ሥ ዘመን)
2. የፊልም ማባዣ/Duplicator (በደርግ ዘመን)
3. የኤሌትሪክ ምጣድ (በደርግ ዘመን)
4. እንጀራ መጋገሪያ መቁረጫ እና ማሸጊያ ማሺን (ፓትንት ከሌላ ሰው ጋር መጋራት አለብህ በመባላቸው የቀረ)
5. በአ.አ ይታዩ የነበሩ ምስላቸውን በየደቂቃው የሚቀያይሩ ቢል ቦርዶች (Prisma vision billboards)
6. የአማርኛ ንግግርን ወደጽሑፍ የሚቀይር የኮምፒውተር ፕሮግራም (በጊዜው ፈላጊ በማጣቱ በጅምር የቀረ)
7. ታዋቂው ስንዝሮ አኒሜሽን (የመጀመሪያው አኒሜሽን በኢትዮጲያ)
8. የመጀመሪያው በኢትዮጲያ የተመረተው አሻንጉሊት (ስንዝሮ አሻንጉሊት)
9. በቅርቡ ደግሞ የእምቦጭ መጥረጊያ ማሽን ለማዘጋጀት ሲደክሙ እንደነበር ይታወቃል።

እንደተገኘው ዜና ከሆነ አቶ ግርማ ከሚኖሩበት አሜሪካ ወደባሕር ዳር በሄዱበት የእኅታቸው ልጅ በስለት ከወጋቸው በኋላ ወደሆስፒታል ተወስደው ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

ቀብራቸውም ዛሬ በባሕር ዳር መፈጸሙን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ነፍስ ይማር! ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጣቸው!