የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አደገኛ የጥፋት ንግግሮችና አስተሳሰቦች! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው )

ከሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

የሆነ ጥሩ ያልሆነ ነገር ይሸተኛል፡፡ ወያኔ በቅርቡ ከመቸውም ጊዜ በከፋ መልኩ አውሬ ሆኖ ሊመጣ እንደሚችል እየታየኝ ነው፡፡ ይሄንን እንድል ያደረገኝ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለትግሮቹ የተናገሯቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ወያኔ ዐቢይን አፈንጋጭ አስመስሎ በማስተወት ብዙ ሊጠቀምበት ይችላል የሚል ግምት ነበረኝ፡፡

ምን እንደተፈጠረ አላውቅም በዚህ በትግራዩ ስብሰባ ላይ በግልጽ እንደታየው ወያኔ በዚህ አጭር ጊዜ የዐቢይን የከፋ ወያኔያዊ አስተሳሰብ ከፍቶ በማሳየት ተታለው በዐቢይ ላይ ብዙ ተስፋ ጥለው የነበሩ ዜጎችን ቅስም በሚሰብር መልኩ ነገሮችን ግልጽ ያደርጋል ብየ በፍጹም አልጠበኩም ነበረ፡፡ እዚያ ስብሰባ ላይ የተሰነዘሩ ሐሳቦች በሙሉ የወያኔን አቅድና ፍላጎት ያንጸባረቁ ሐሳቦች ናቸው፡፡ የፖለቲካ እስረኞች መፈታት ፍጹም ስሕተት መሆኑን የሚገልጽ ሐሳብ ሳይቀር ተንጸባርቆ የጋለ ጭብጨባ ተችሮታል፡፡

ዐቢይ በዚህ ስብሰባ ላይ “ጊዜ እንስጠው!” እያሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚጠብቁትን ለውጥ እስኪያደርግ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይቀር ለመጠበቅ ዝግጁ የነበሩ ተስፈኛ የዋህ ዜጎችን ፈጽሞ ያልተጠበቁ ነገሮችን በመናገር ኩም አድርጎ ምኞትና ተስፋቸው ከንቱ መሆኑን አረጋግጦላቸዋል፡፡

ለምሳሌ ሕዝብ ስንት የወያኔን አረመኔያዊ ግፍ ከአርባ ዓመታት ለበለጠ ጊዜ ያህል የተቀበለበትን፣ ስንት መራር ዋጋ የተከፈለበትን፣ እንደ ሕዝበ ውሳኔ ያለ አንድም ዓይነት ሕጋዊ አኪያሔድ ሳይፈጸም በማን አለብኝነትና በሕገወጥ መንገድ ወደ ትግራይ እንዲከለሉ በመደረጋቸው የተፈጠረውን “የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ!” የሚባል ነገርን ጨርሶ ማየት መስማትና ማስተናገድ እንደማይፈልግ፦

“….እኔ የምመኘው ወልቃይት አካባቢ፣ አርማጭሆ አካባቢ ያሉ ዳያስፖራዎች ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ነው፡፡ መጥተው ሕዝቡን እንዲያዩት፣ የሕዝቡን ኑሮ እንዲያዩት፣ የሕቡን ችግር እንዲያዩት፡፡ ሕዝቡ እያለ ያለው መንገድ፣ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ፣ መብራት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ያለው አጀንዳ የሕዝብ አጀንዳ አለመሆኑን ሲያውቁ ብዙዎቹ ሳያውቁ የሚደናገሩት ከሕዝብ ጋር ይሆናሉ የሚል እምነት አለኝ….”

በማለት የአደባባይ ምሥጢር የሆነን የወልቃይት ሕዝብ ንቅናቄን ሸምጥጦ በመካድ እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ የሕዝብን ልብ አድምቷል፣ ፀረ አማራ አቋም አመለካከቱን አሳውቋል፣ የግፈኛ አረመኔ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀለኛ ትግሮች አሽከርነቱን ሎሌነቱን ጥርት አድርጎ አሳይቷል፣ የዝርፊያ የውንብድና ደጋፊ አገልጋይ መሆኑን አረጋግጧል፣ የሕዝብን ችግር እንደሚፈታ ቃል የገባውና የተናገረው ማስመሰል መሆኑን አጋልጧል፡፡

ዐቢይ ትግራይ ላይ የተናገረው ነገር ሁሉ ያሳየው ዐቢይ ጉዳይ ቢኖር የሱና የለማ ቡድን ወይም ኦሕዴድ ከወያኔ ጋራ ሆኖ በአማራ ሕዝብና ጥቅም ላይ ምን ያህል አደገኛ ቁማር እየቆመሩና እየተመሳጠሩ መሆናቸውን ነው፡፡ አማራ ሆይ! እባክህን ፈጥነህ ንቃ! ተው ተበላህ!!!

አንዱን ዓየ ሁሉን ዓየ እንዲሉ ከዚህ የዐቢይ ፀረ አማራ አቋም አስተሳሰብ ተነሥተን ዐቢይ ለወያኔ/ትግሬ ሲል ሃቅን በአደባባይ ክዶ የአማራ ሕዝብን ጩኸት በኢፍትሐዊነት ለግፈኛና ወንበዴ ትግሮች በማድላት ተገቢ ምላሽ ላለመስጠት መቁረጡን ይፋ ካደረገ እቀርፋለሁ ብሎ የተናገረው የሰብአዊ መብት ረገጣን፣ ዝርፊያን፣ ሙስናን፣ ብልሹ አሥተዳደርን፣ አፈናን፣ ጠተያቂነት መጥፋትን፣ የሕግ የበላይነት አለመኖርን፣ የፍትሕ እጦትን ወዘተረፈ. ሁሉ ሕዝብን ለመደለል የደሰኮረው እንጅ የሚቀረፉ አለመሆናቸውን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ወያኔ በተፈጥሮው ያለ እነዚህ መተላለፎችና ወንጀሎች ሕይዎት ኖሮት መኖር መንቀሳቀስ አይችልምና ነው፡፡

አንዳንድ ቂሎች ግን አሁንም “ዐቢይ እዚያ አዳራሽ ውስጥ ለትግሮች የተናገረውን ሁሉ የተናገረው ትግሮች በዐቢይ ላይ ጥርጣሬ ስላላቸውና በዐቢይ መመረጥ ድንጋጤ ላይ ስለወደቁ ለማረጋጋት ብሎ ነው ማለት የሌለበትን ነገሮች ሁሉ የተናገረው!” በማለት ለመጃጃላቸው የራሳቸውን አስቂኝ ምናብ እየፈጠሩ መጃጃላቸውን ቀጥለውበታል፣ ለወያኔ ደንበኛ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ እየሠሩለት ይገኛሉ፡፡ እኔ እነኝህ ሰዎች ወይ ስውር የወያኔ ካድሬ (ወስዋሽ) ይሆናሉ እንጅ በጤናቸው እንዲህ ፈጦ የሚታይን ነገር መረዳት መገንዘብ ይሳናቸዋል ብሎ ለማለት የሚከብድ ይመስለኛል፡፡

ዐቢይ የመለስን ያህል ባለ ሙሉ ሥልጣን ቢሆንና “በዐቢይ መመረጥ ትግሮቹ ደነገጡ!” ቢሉን ባመንናቸው ነበረ፡፡ ይሄ ዕድል ለዐቢይ በምንም ተአምር ቢሆን እንደማይኖረው እየታወቀ አስቀድሞ ወያኔ ዐብይን በሕዝብ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ ፀረ ሕወሓት አስመስሎ በሠራው ሐሰተኛ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ተጃጅለው ዛሬም ስንት ዓይን ገላጭ ነገሮችን ዕያዩና እየሰሙ በመጃጃሉና በማጃጃሉ መቀጠላቸው እጅግ የሚያስገርም ነው፡፡ በማን ዘመን የደነቆረ ምን እያለ ይኖራል እንደተባለው ነው የሆነው፡፡

ሌላው የገረመኝ ነገር ደግሞ ኮሎኔል ዐቢይ የወያኔ ሠራዊት አባል እንደነበረ፣ የወያኔ አፋኝና ሰቆቃ ፈጻሚ አገዛዝ የደኅንነት ክፍል ዋና ሹም እንደነበረ እረስተው ወያኔ ሠማዕታት የሚላቸውን ቅሱፋንና የሞቱለትን ዓላማ “ዐቢይ ያደንቃል ክብር ይሰጣል ብለን አልጠበቅንም ነበር!” ማለታቸው ነው፡፡

ይሄ የሚያሳየው ወያኔ የኦሮሞን ሕዝብ ከኦነግ ደጋፊነት አውጥቶ የኦሕዴድ ደጋፊ ለማድረግ በማሰብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ የለማን ቡድን ወይም ኦሕዴድን አለኝታው አድርጎ እንዲያስበው እንዲቀበለው ለማድረግ ፀረ ሕወሓት አስመስሎ ሲያስተውናቸው የቆየው ድራማ ምን ያህል የተሳካለት እንደነበረ ነው፡፡

ከላይ ወያኔ ሠማዕታት የሚላቸውን ታጋዮቹን ቅሱፋን ስል የጠራሁበት ምክንያት ከአራት ዓመታት በፊት በዕንቁ መጽሔት ላይና በድረ ገጽ “የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉ የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን?” በሚለው ጽሑፌ ላይ እንደገለጽኩት፦

“”….በበኩሌ እነኝህን ታጋዮች ሠማዕታት ብዬ ልዘክራቸው ሳስባቸው ክብር ልሰጣቸው የምችለው ኢትዮጵያንና ጥቅሞቿን በተመለከተ አሁን በሕይወት ካሉት የሕወሓት ኢሕአዴግ ባለሥልጣናትና ታጋዮች የተለየ ማለትም የኢትዮጵያንና የሕዝቧን ጥቅም፣ ክብር፣ ሉዓላዊነት የሚያስጠብቅ አቋም የነበራቸው እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ከቻልኩ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ያለፉ ታጋዮች በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ አሁን በሕይዎት ካሉት የተለዩ ሊሆኑ እንደማይችሉ አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከሕወሓት ኢሕአዴግ ታሪክ እንደምንረዳው አሁን ሥልጣን ይዘው ያሉት የፈጸሙትና እይፈጸሙት ያለው ክህደት፣ የሠሩትና እይሠሩት ያለው በደል፣ ያደረጉትና እያደጉት ያለው ግፍ ሁሉ ለምሳሌም ኤርትራን ማስገንጠል፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንድነት በብሔር ብሔረሰቦች መብት ሽፋን እንዳልነበረ አድርጎ ማፈራረስ፣ የሀገሪቱን ታሪክ መካድና በመቶ ዓመታት ብቻ ማሳጠር፣ ነፍጠኛ ትምክህተኛ ወዘተ እያሉ በማሸማቀቅ የዜጎችን የሀገር ፍቅር ስሜት ማጥፋት፣ በተይ አማራውን ሕዝብ በጠላትነት በመፈረጅ እንዳያንሠራራ አድርጎ መሥበር ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እነዚህን ድርጊቶች እዚያው በረሐ እያሉ ጀምሮ በዐቅድ ደረጃ ይዘውት የነበርና የሞቱ ታጋዮቻቸውም ይሄንን አምነውበት ለስኬታማነቱ ሲታገሉ የሞቱ በመሆናቸው በሕይዎት ቢኖሩ ኖሮ አሁን በሕይወት ካሉትና ሀገር ከሚያምሱት የተለዩ ሊሆኑ እንደማይችሉ እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡ በመሆኑም የእነዚህ ሙታን ሠማዕትነታቸው ለሕወሓት ኢሕአዴጋዊያን እንጅ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ አይደለም ማለት ነው፡፡ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧስ ምንድን ናቸው ያልን እንደሆነ ቅሱፋን የሚለው ቃል ማንነታቸውን የሚገልጽ ይሆናል፡፡ ደማቸውም ለልማት ሳይሆን ለጥፋት የፈሰሰ በመሆኑ ደመ ከልብ ነው፡፡ ከዚህም አንጻር ለእነሱ መታሰቢያ ተብለው የቆሙት ሐውልቶች ዕድሜ ይህ “መንግሥት” እስካለ ጊዜ ድረስ ብቻ መሆኑ እርግጥ ነው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ሀገሪቱ እንደ አሁኑ ሁሉ ተገዳ ካልሆነ በስተቀር ወዳና ፈቅዳ ጠላቶቿን ልታስብ ልትዘክር የምትፈቅድበትና የምትገደድበት እንዳችም ምክናያት ስለሌለና ስለማይኖር!…..”” ብየ ስለማምን ነው፡፡

ሙሉውን ጽሑፍ ይሄንን ሊንክ (ይዝ) ከፍተው ሊያነቡ ይችላሉ፦

ሌላው ያስደነቀኝ ያስገረመኝ ነገር ትግሮቹ ትግሬ (ባሪያ፣ አገልጋይ) የሚለውን ማንነትታቸውን በግልጽ የሚናገረውን ስማቸውን ለመሸሽ በየጊዜው አንዴ ትግራዋይ አንዴ ተጋሩ እያሉ ስማቸውን ለመሸሽ መከራ የሚያዩትን፣ በማንነት ቀውስና በሥነልቡና ችግር የተጎዱትን፣ በበታችነት ስሜት የታመሙትን የትግሬን ሕዝብ ሥነልቡና ለማከም ዐቢይ የሌላቸውንና የትግሬ ያልሆነን የአማራን ታሪክና ገድል እያነሣ ማሸከሙ፣ የባንዳነትና ጠንቀኝነት አሳፋሪ የማንነት ታሪካቸውን እየሸሸገ መቀበጣጠሩ ነው እጅግ የገረመኝ፡፡ እሱ ስለሰጣቸው የነሱ የሚሆን ይመስላቸዋል ማለት ነው??? አየ የበታችነት ሕመም እንዴት ያስቃዣል ባካቹህ???

የአማራ (የአክሱማውያን) ባሪያ የነበረ ሕዝብ ዮዲት ጉዲት በአርባ ዓመት ዘመቻዋ አማራን ከአክሱምና አካባቢው በማጥፋቷ ወደ ኋላ ላይ ትግሬ ወይም ትግራይ ተብሎ ተጠርቶ የቀረውን የሀገራችንን ክፍል ወርሰው መቅረታቸው ለታሪክ ዝርፊያው በደንብ ነው የተመቻቸው፡፡

ሌላውና እጅግ የደነቀኝ ነገር ደግሞ ዐቢይ የመለስን ባዶና ዘረኛ ስብከት ተውሶ የተናገረው ነገር ነው፡፡ ቆይ ግን ዐቢይ ትግሬን አንደኛ ሲያደርግ ኦሮሞን ሌሎቹንስ ስንተኛ ስንተኛ አድርጎ ይሆን??? ፣ ትግሬን ወርቅ ሲያደርግ ኦሮሞን ሌሎቹንስ ምን ምን አድርጎ ይሆን??? ወራዳና ባንዳ የትግሬን ሕዝብ ብረት ሲያደርግ በአይበገሬ መንፈስ ተነግሮ ሊያልቅ በማይችል መሥዋዕትነትና ጽናት ለዚህች ሀገር አንድነት፣ ነጻነት፣ ሉዓላዊነትና ህልውና እራሱን እንደሻማ ሲያቀልጥ የኖረውን ብርቅና ድንቅ የአማራን ሕዝብ ምን ብሎ ሊገልጸው ይሆን???

አሁን ታዲያ ይሄንን የወያኔ ተናጋሪ እንስሳ እንዴት ብለን ነው ሰው የምንለው??? የዚህን ያህል ራሱን የበታች እንደሆነ አሳምኖ ለማገልገል ያዘጋጀን የ21ኛው መቶ ክ/ዘ አስነዋሪ ባሪያ እራሱን ነጻ ሳያወጣ፣ ለራሱ ዕኩልነቱን ሳያምንና ሳያረጋግጥ እንዴት ነው ታዲያ ለእኩልነት፣ ለፍትሕ፣ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲ (ለመስፍነ ሕዝብ) ቀናኢ፣ ታማኝና ትጉ አገልጋይ ይሆናል ብላቹህ የምትጠብቁት???

ያለው ነገር ሁሉ እውነት ሆኖ የተናገረውን ቢናገር እኮ ብዙ የሚገርም ባልሆነ ነበር፡፡ የሚለው ነገር ሁሉ ሐሰት እንደሆነ ልቡናው እያወቀ ራሱን ለሐሰት ማስገዛቱ እኮነው የሰውየውን ሰብእና እጅግ የወረደ ያደረገብኝ! እግዚኦ!!! ከእንዲህ ዓይነት ውርደትና ዝቅጠት መድኃኔዓለም ይሠውረን!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
[email protected]