የኢሕአዴግ ካቢኔ ይፋ ሆነ። የኢሕአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አዳዲስ ሚኒስትሮቻቸው ታወቁ ።

የኢሕአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አዳዲስ ሚኒስትሮቻቸውን እየታወቁ ነው። በዚህም መሰረት የኦሕዴዱ ሞቱማ መካሻ የመከላከያ ሚኒስትሩን ቦታ ሲያዙ ሲራጅ ፈርጌሳ ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት ይዘዋወሩና የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ደግሞ የነገሪ ሌንጮን የኮሚኒኬሽን ሚኒስትርነት ቦታ ይይዛሉ። ሽፈራው ሽጉጤ ሚኒስትር የተፈጥሮ ሃብትና የእርሻ\የግብርና ሚኒስትር ሆነዋል :: የግብርናና የተፈጥሮ ሃብት እንዲሁም የ አሳና የእንሰሳት ሚኒስተሮች ለመን ተቀናጁ ለምን አይለያዩም የሚል ጥያቄ በምክር ቤት ውስጥ ተነስቶ እንደ ትልቅ አጀንዳ ጊዜ ተገድሎበታል።

  1. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የግብርና እና የእንስሳት ሚ/ር
  2. አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ የትራንስፖርት ሚ/ር
  3. ዶ/ር ሂሩት ወ/ማሪያም ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር
  4. አቶ ተሾሞ ቶጋ የመንግስት ልማት ሚ/ር
  5. አቶ ዑመር ሁሴን ኦባ በሚኒስትር ማዕረግ ገቢዎችና ጉምርክ
  6. ወ/ሮ ኡባ ሙሀመድ ሁሴን የመገናኛ ና ኢንፎርሜሽን ሚ/ር
  7. ዶ/ር አምባቸው ሲሳይ የኢንዱስትሪ /ሚ/ር
  8. አቶ ሞቱማ መቃሳ የሀገር መከላከያ ሚ/ር
  9. ወ/ሮ አሚና አልየ የባህልና ቱሪዝም ሚ/ር
  10. አቶ አህመድ ሽዴዴ የኮ/ሚ/ር
  11. አቶ ጃንጥራር አምባው የከተማ ልማትና ቤቶች ሚ/ር
  12. አቶ መለሰ አርቦቦ የማዕድንና ኢነርጅ ሚ/ር
  13. አቶ ብርሀኔ ጸጋዬ ጠቅላይ አቃቢ ህግ
  14. ወ/ሮ ያለም አስፋው የሴቶችና ህጻናት ሚ/ር
  15. አቶ መላኩ አለበል የንግድ ሚ/ር
  16. ዶ/ር አሚር አማን የጠና ጥበቃ ሚ/ር ተደርገው ተሹመዋል።

ለስድስት ዓመታት የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሆነው የሰሩትን አቶ አባዱላ ገመዳን በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል የነበሩት አቶ አሰፋ አብዩ ከቦታቸው ተነስተው አቶ ያሬድ ዘሪሁን ኮሚሽነር ጄነራል ሆነው ቦታውን ተረክበዋል።

ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያቸውን እንዳቀረቡ በተነገረላቸው ሜጀር ጄነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ ምትክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተተክተዋል።

ዶ/ር በቀለ ቡላዶ የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በመሆን ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያቸውን እንዳቀረቡ የተነገረላቸውን የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ቦታ ተረክበዋል። ዶ/ር በቀለ ኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል።

ወ/ሮ ደሚቱ ሀምቢሳ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር።

በተጨማሪም ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ።

አቶ ሞገስ ባልቻ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የጥናትና ፐብሊኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ።

አቶ አህመድ አብተው በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር።

አቶ ዓለምነው መኮንን በሚኒስትር ማዕረግ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንት።