ድምፃዊ ታምራት ደስታ በሐኪሞች ንዝህላልነት ጊዜው ያለፈበት መድሐኒት ተወግቶ እንደሞተ ተረጋገጠ

የአስክሬን ምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ

እስከመቼ በህክምና ስህተት….?!

የራሱን መኪና እያሽከረከረ የቶንሲል ህመሙን ለመታከም ሄዶ ድንገት ለምን ሞተ? ከሞቱ ይልቅ አሟሟቱ በጣም የሚያሳዝን አርቲስት ታምራት ደስታ የሞተው በህክምና ስህተት እንደሆነ ተረጋገጠ።

ለቶንሲል ተብሎ የተሰጠው መድሃኒት ccp የተመረዘ ማለትም አመተ ምህረት ካለፈበት ወደ አሲድነት የመለወጥ ባህሪ ያለሁ ሲሆን የተሰጠው መድሃኒት ccp የተባለ አመተምህረቱ ያለፈበት በመሆኑ የተመረዘና እንዲሁም የልብ ምትን በሶስት እጥፍ እንደሚጨምር ተረጋግጧል።

በጳውሎስ ሆስፒታል በአስክሬኑ ላይ በተደረገ ምርመራ ውጤቱ እንዳሳየው መዳኒቱ አናቱ ላይ ወጥቶ አርቲስቱ ccp የተባለውን ግዜው ያለፈበት መድሀኒት ከተወጋ ከ30 ደቂቀ በኋላ ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።

ከዚህ በፊት በተፈጠሩ የህክምና ስህተት የብዙ ሰዋች ህይወት እንደ ዋዛ አልፏል።

የ6 አመት ህፃን ሊገረዝ ሆስፒታል ገብቶ የቁስል ማድረቂያ መድሃኒት ሰጠን ብለው የአስክሬን ማድረቂያ ወግተው የገደሉት በህምክና ስህተት እንደነበር ከአመታት በፊት አንብበናል።

ሆዷን ቆርጧት የሆድ ቁርጠት መድሃኒት ልትገዛ ለሄደች አንዲት ምስኪን ሴት ለሚጥል በሽታ የሚሰጠውን መድሃኒት ሰጥተው የሰውነት ቆዳዋ ተላልጦ ሞታለች። በየጊዜው ብዙ ያልተሰሙ፣ እንዲሰሙ ያልተፈለጉ ብዙ የህክምና ስህተቶች ወገኖቻችንን ሲጨርሱ ኖረዋል።

ሊድን የሄደን ሰው እየገደሉ በስህተት ነው!” እያሉ ብዙዎች ታልፈዋል።

የዘርፉ ባለሙያዎች በእጃቸው የያዙት ሮቦት አይደለም! ክቡሩንና ተመልሶ የማይገነኘውን የሰው ነፍስ እንጂ። እውቀቱ ከሌላቸው አርፈው ሌላ ነገር ይስሩ። በሰው ህይወት መቀለድ ይብቃ!!!

ምንጭ etcm©news