በወልቃይት ሴቶች ላይ የሚፈፀም ግፍ

በወልቃይት ሴቶች ላይ የሚፈፀም ግፍ!

~”ወንዶች ጥርግ ብላችሁ ጥፉ። እኛ የምንፈልገው መሬታችሁን፣ ሚስቶቻችሁን እና ሴት ልጆቻችሁን ነው” የትግራይ ባለስልጣናት ለወልቃይት ተወላጆች

ወልቃይትን የሚፈልጉት መሬትና ሴቶችን እንደሆነ የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በአባላቱ ፊርማ ታህሳስ 7/2008 ዓም ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት ያቀረበው አቤቱታ በግልፅ ያሳያል። ከሚቴው በአቤቱታው እንደሚከተለው አቅርቧል።

1ኛ አቶ ካልአዩ አሰፋ የተባለ የወልቃይት ዋና አስተዳዳሪ የሆኑ የአቶ ብርሃኑ ካህሳይ ባለቤት ወይዘሮ ትግስት መለሰን አስገድዶ ወልዶባት፣ ከትዳሯ ተፋትታለች።

2ኛ አቶ ሰለሞን የተባለ የወልቃይት ፖሊስ አዛዥ አቶ አለማው ጉዕይን አስሮ ባለቤቱን ወይዘሮ አዜብ አዛናውን አስገድዶ ወልዶባታል።

3ኛ በትምህርት ቤት ብዙ መምህራን ብዙ የወልቃይት ወጣት ሴት ተማሪዎችን አስገድደው ክብረ ንፅህና በመገርሰስ እና በመድፈር በሕግ ቢጠየቁም “ደግ አደረጉ” የሚል መልስ ከሚመለከተው አካል በማግኘታቸው አስገድዶ መድፈርን እየቀጠሉበት ይገኛሉ።

ይህ ድርጊት በአንድ ወቅት አቶ ማዕረግ “ወልቃይት የትግራይ ናት፣ እመኑ!” ብሎ በጠየቀበት ወቅት ሕዝብ “አናምንም” ብሎ ቢቃወም “ወንዶች ጥርግ ብላችሁ ጥፉ። እኛ የምንፈልገው መሬታችሁን፣ ሚስቶቻችሁን እና ሴት ልጆቻችሁን ነው” ብሎ ሲናገር አለቃ ፀጋዬ (የቀድሞው የትግራይ ርዕሰ መስተዳደር) ነበሩ። ይህ በአሁኑ ወቅት በተግባር እየተገፀመ ነው። ይህ ተጨባጭ መረጃ ሲሆን በቀጣይ ፍትህ እስክናገኝ የደረሱትን በደሎች ለሕዝብ እናደርሳለን!

(መረጃው የወልቃይት ኮሚቴ ለተለያዩ ተቋማት ታህሳስ 7/2008 ዓም ካስገቡት ማመልከቻ የተወሰደ ነው)