በህወሓት ደህንነት ቢሮ የተጠኑና የሕወሓትን ግብ የሚያሰፈፅሙ ተሿሚዎች በየአመቱ እየተቀያየሩ ምንም ሳይሰሩ የሀገርን ሀብት ያባክናሉ ።

ፖለቲካ የማይገባው የኢሕአዴግን ሹመት አይቶ ሕወሓት የለችም ሲል ምስጋናውን ያዥጎደጉዳል ፤ መጀመሪያ ደረጃ በሹመት እየተንበሸበሹ ያሉት ከሕወሓት በላይ ሕወሓት ሆነው ለመታየት ወንጀል ሲሰሩ የኖሩ አደርባዮች ናቸው ።

ቁልፍ የሆኑ ቦታዎች በሕወሓቶች የተያዙ ተይዘዋል። ምንም አዲስ ነገር የለም፤ በህወሓት ደህንነት ቢሮ የተጠኑና የሕወሓትን ግብ የሚያሰፈፅሙ ተሿሚዎች በየአመቱ እየተቀያየሩ ምንም ሳይሰሩ የሀገርን ሀብት ያባክናሉ ። በበታች ሹማምንት ስራውን እያሰራ ለፊርማ የሚጠራቸው ሹማምንቱ አንድም የረባ ስራ ያልሰሩ ቢያኮርፉ የክስ ሰነድ የሚመዘዝባቸው ተሿሚዎች ናቸው ፤ ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎች ባለፈው ሳምንታት ያደረጉትን ዥዋዥዌ አይቶ በቀላሉ የሚጠመዘዙ ስትራቴጂ አልባዎች ሲል ገልጿቸዋል ።

የደህንነቱና ወታደራዊው መዋቅር (መሾምና መዋቅር መምራት ኢሕአዴግ ቤት ይለያያል ) በሕወሓቶች መዋቅር ከላይ እስከተች ተይዞ መላወሻ ማግኘት አልተቻለም ፤ ከሁሉም ቀድሞ ይህ መዋቅር ተበጣጥሶ በሕዝባዊ መዋቅር ሊተካ ይገባል ፤ ለሐገርና ለሕዝብ አደጋ የሆኑ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስት ሲናኙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ። ይህ ስርአት ከስሩ ተነቅሎ ካልተጣለ በስተቀር ነገሮች ሁሉ ወደባሰ መንገድ እየተጓዙ መሆኑ በርካታ አመላካች የፖለቲካ ሒደቶች ከአገዛዙ ይፈልቃሉ ። #MinilikSalsawi