ደህንነቶች ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ፖስፖርቱን ቀምተው ከሀገር እንዳይወጣ ከልክለውታል

ደህንነቶች የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፖስፖርቱን ቀምተው ከሀገር እንዳይወጣ ከልክለውታል።

እስክንድር ነጋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አምስተርዳም በሚያደርገው ስብሰባ ላይ በክብር እንግድነት ተጋብዞ ለመሔድ አዲስ አበባ ኤርፖርት እንደደረሰ በደህንነቶች ፓስፖርቱን ተነጥቆ ከሐገር እንዳይወጣ ተከልክሏል፡፡

እስክንድ ለባለቤቱ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ገልፆታል። “ዕቃዬን አስገባኹ። ቦርዲንግ ፖስ ካላፈ በኅላ ኢምግሬሽን ለማለፍ ስሄድ፣ አንዲት ሴት ፖስፖርቴን ተቀብላኝ ወደ ቢሮ ገባች። ለብቻህ ተቀመጥ አሉኝ። ግማሽ ሰዓት ያህል ከጠበኩ በኅላ አንድ ሰው መጥቶ ኢምግሬሽን ዋናው ቢሮ ሄደህ ማናገር ትችላለህ ተብዬ ፖስፓርቴን ቀምተው መልሰውኛል።”

እስክንድር በሰላማዊ ትግል ውስጥ የሚገኝ ትንታግ ብእረኛ ሲሆን በተደጋጋሚ አገዛዙ ግፍ እየፈፀመበት ነው። ከዚህ ቀደም በዶ/ር መረራና በቴዲ አፍሮ ላይ ይህ ግፍ ተፈፅሟል።

እስክንድር በኤርፖርት የገጠመውን ሲናገር ፖስፖርቴን ሲነጥቁኝ “ይሄ ነገር እታች ያላችሁ ወስናችሁ ከሆነ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ስለሚፈጥር የበላይ ጠይቃችሁ ተመለሱ አልኳቸው”

እነሱም “የበላይ ትዕዛዝ ነው” አሉኝ

“እርግጠኛ ናችሁ?” ስል ደግሜ ጠየኳቸው…

“እርግጠኛ ነን የበላይ ትዕዛዝ ነው” አሉኝ በድጋሚ

ፍትህ ለእስክንድር ነጋ! #MinilikSalsawi