የጎንደር ህዝብ ለፍትህ ሺዎችን የገበረ ህዝብ ነው ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

“ይህ ዛሬ በደመቀ ሁኔታ በአክብሮት የተቀበለዎት የጎንደር ህዝብ ከጥንት እስከ ዛሬ ለፍትህ መስዋዕትነት እየከፈለ የመጣ ህዝብ ነው። ለፍትህ ሺዎችን የገበረ ህዝብ ነው። አሁንም እርስዎ በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህና ነፃነትን ለማስፈን በሚያደርጉት ትግል የጎንደር ህዝብ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል የማያቅማማ መሆኑን በሙሉ እምነት በታላቅ ኢትዮጵያዊ አክብሮትና ኩራትም ጭምር ነው ”
ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የጎንደር ሕዝብ ጠ/ሚኒስተሩን ጨምሮ በከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ላይ በዝምታ ተቃውሞውን ገለፀ!

ዛሬ ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ/ም ከረፋድ 4:25 ሲሆን ጎንደር ፋሲለደስ ስታዲዬም ጠ/ሚ አብይ አህመድ፡ ገድ አንዳርጋቸው፡ ደመቀ መኮነን ሲገቡ በግዳጅ ብሎም በአበል እና በአንዳንድ ጥቅማ ጥቅም የገቡ አርሶአደሮችና የከተማው ነዋሪዎች ልክ እንደተመካከሩ ከመቀመጫቸው ባለመነሳትና ምንም አይነት ድምፅ ባለማሰማት በዝምታ ተቃውሞውን ገልፃል፡፡

አስተባባሪዎች በከፍተኛ የድምፅ ማጉያ በመጠቀም፡ “የተከበሩ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በመግባት ላይ ናቸው” ሲል የሕዝቡ ምላሽ ዝምታ ሆነ፡ አስተባባሪው ቀጠለ “የኢፌዴሪ ም/ጠ/ሚ የተከሩ አቶ ደመቀ መኮነን በመግባት ላይ ናቸው” ሲል አሁንም ሕዝቡ ምላሹ ዝምታ ሆነ፡፡ አሁንም አስተባባሪው ቀጠለ “የአ/ብ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር የተከሩ አቶ ገድ አንዳርጋቸው በመግባት ላይ ናቸው” ሲል አሁንም የሕዝቡ ምላሽ ዝምታ ሆነ፡፡ በመሆኑም በግዳጅም ይሁን በማታለል የገባ በሚገርም መልክ ተቃውሞውን በዝምታ የገለፀ ሲሆን እነዚህ ባለስልጣናት እጃቸውን ቢያውለበሉቡም ከሕዝብ ያገኙት ምላሽ ዝምታ ነው የሆነው፡፡ በሕዝቡ ተቃውሞ የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል ፡፡ ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን እንገልፃለን።