መቀሌ ላይ ስለ ወልቃይት በተናገሩት አፍረናል፣ እኛ ከእርስዎ ይህን አንጠብቅም ነበር።

“አፍረናል!” አቶ አታላይ ዛፌ ለዶ/ር አብይ

“መቀሌ ላይ ስለ ወልቃይት በተናገሩት አፍረናል፣ እኛ ከእርስዎ ይህን አንጠብቅም ነበር። ……የወልቃይት ማንነት ጠያቂዎች መካከል እኔ አንዱ ነኝ፣ ብዙዎች የታሰሩበት፣ የተገደሉበት ነው። ጥያቄው የዳያስፖራ አይደለም”

የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባል አቶ አታላይ ዛፌ ከዶ/ር አብይ ጋር በነበራቸው ግንኙነት የተናገሩት ነው ብሎ ስብሰባው ላይ የነበረ ሰው የነገረኝ።

አቶ መላኩ ፋንታ የተከሰሰበትን አሳዛኝ ክስ አንስተው መፈታት እንዳለበትም የጠየቁ ተሳታፊ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

ዶ/ር አብይ “የወልቃይት ጉዳይ በፌደሬሽን ምክር ቤት ይታያል” እንዳሉ ተሰምቷል።

ዶ/ር አብይ አቶ አታላይን እና ሌሎች የኮሚቴ አባላትን አስጠርተው እያነጋገሯቸው ነው!

“መቀሌ ላይ በተናገሩት አፍረናል……” ሲሉ ዶ/ር አብይ ላይ ቅሬታ ያቀረቡትና ስለ ወልቃይት ጥያቄ ያብራሩትን የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባል አቶ አታላይ ዛፌን ዶ/ር አብይ ብቻቸውን አስጠርተው እያነጋገሯቸው እንደሆነ የስብሰባው ተሳታፊዎች ገልፀውልኛል!

ጠቅላዩ የሰጡት ምላሽ ስለ ወልቃይት

የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ በህግ አግባብ ሊፈታ እንደሚችል ህዝቡ ማመን አለበት ፡፡ ህገ መንግስቱ ይህን ጉዳይ ሊፈታ ይችላል፡፡ በቀጣይም ከወልቃይት ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አደርጋለሁ ብለዋል፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ በመወያየት ያሉ ጥያቄዎች መመለስ እንችላለን፡፡ ዋናው ነገር በዚህ ሂደት ውስጥ ሀይል የተቀላቀለበት እና ወደ ቁርሾ በሚያስገባ መንገድ መሆን እንደሌለበት ህዝቡ ሊያውቅ ይገባል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ጥያቄዎች

  • በጎንደር በኢንዱስትሪ መንደር አለመካተቱ ኢፍትሀዊ ነው
  • ጣና ሃይቅ በእንቦጭ ሲጠቃ የፌደራል መንግስት ችግሩን ለመፍታት ምን ተሰራ?
  • በእስር ላይ የሚገኙ የደርግ ባለስልጣናት ጭምር ይቅር ተብለው ሊፈቱ ይገባል
  • የአማራ ክልል ከሱዳን ጋር ያለው ድንበር ችግር አለበት መፍትሄ ሊሰጠው ይገባዋል
  • ሙስና ስር ሰዷል ባለስልጣናት ፎቅ ቤት መኪና ሌሎች ሃብቶች ሲያካትቱ የሀብቱ ምንጭ ከየት እንደመጣ መጣራት አለበት
  • ኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ ያስፈልጋታል ይህን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይዘው ሊፈፅሙት ይገባል
  • ከፍተኛ አመራሩ ህዝቡ ጋር ወርዶ መስራት አለበት
  • የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለአንድ ወገን ያደላ ሳይሆን ህዝባዊ ወገንተኝነትን የተላበሰ መሆን አለበት