ወያኔ በላስ ቬጋስ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ላይ አዲስ ጥቃት ከፈተ

በዛሬው እለት በደረሰን መረጃ መሠረት ላስ ቬጋስ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን በህጋዊው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ ስር የሚተዳደረውን ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከምዕመናን ነጥቆ ለወያኔ የማስረከብ ሂደት በስውር ሲካሄድ ቆይቶ አሁን አንድ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጾልናል። በዚህም መሠረት ሲሳይ ኪዳኔ በተባለ የወያኔ ተላላኪ አጋፋሪነትና በጥቅም በተገዛው ተሻገር ከልካይ ግብር-አበርነት የቤተክርስቲያኑንን የጎደሉ የሰበካ ጉባኤ አባላት ለማሟላት በተደረገው ምርጫ ለቤተክርስቲያኑ ለበርካታ ዓመታ በተቆርቋሪነት ሲደክሙ የነበሩ ምዕመናን እንዳይመረጡ የማጥላላትና ስም የማጥፋት ዘመቻ እንደተካሄደባቸው ተገልጾልናል። የወያኔው ወሬ አቀባይ ሲሳይ ከዳኔ ከምርጫው አንድ ቀን አስቀድሞ ከተሻገር ከልካይ ጋር ባካሄደው ህግ ወጥ የቴሌኮንፍረንስ ምዕመናንን በማስፈራራት፣ የውሸት መረጃ በመስጠትና በጎሰኝነት በማሸማቀቅ ድብቅ አጀንዳውን እውን ለማድረግ አንድ እርከን ወደፊት ለመሄድ ችሏል ተብሏል።

በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ እንዲያገለግሉ በምዕመናን የተመረጡት ሲሳይ ከዳኔና ተሻገር ከልካይ በመተዳዳሪያው ደንብ መሠረት ምዕመናን እንዲያገለግሏቸው የጠቆሟቸውን ተወዳዳሪዎች በገለልተኛነት የምርጫውን ሂደት ማካሄድ ሲገባቸው “እከሌን ምረጡ፣ እከሌን አትምረጡ” እያሉ ህገወጥ ቅስቀሳ በቴሌኮንፍረስ ማካሄዳቸው ተግልጾልናል። በዚህም ድርጊታቸው ከአባላት የተሰጣቸውን አደራ በመብላት የግል ፍላጎታቸው እንዲሳካ አድርገዋል።ምርጫው በገለልተኛና በነጻ አስመራጭ ኮሚቴ ስላልተካሄደና በድምፅ ቆጠራውም ላይ የማጭበርበር ድርጊት ተፈጽሞ ሊሆን ስለሚችል አዲስ ምርጫ በቤተክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ነጻና ገለለተኛ በሆኑ አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት እንደገና መካሄድ አለበት የሚሉ ነባር ምዕመን ቁጥራቸው ቀላል እንዳልሆነ ታውቋል።

የሲሳይ ኪዳኔ አላማ ብጥብጥ መፍጠርና ምዕመናን በመከፋፋልና በተለያየ ጎራ በማሰለፍ በሚፈጠረው ክፍተትና ግርግር ቤተክርስቲያኑን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት ነው። ይህም የወያኔ አሰራር በተለያዩ  የአውሮፓ፣ የካናዳና አሜሪካ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ ቤተክርስቲያኖች ላይ ተፈጻሚ መሆኑ ይታወቃል። በተለይም በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በስደት በሚገኘው ሲኖዶስ ስር የሚተዳደር በመሆኑና በርካታ የወያኔ ተቃዋሚ የሆኑ ምዕመናን ሲለሚገኙበት ጭቅጭቅና ንትርክ በመፍጠር ለወያኔ ሾልኮ መግቢያ ቀዳዳ ለመክፈት የተለያዩ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች በስውር ሲካሄዱ መቆየታቸው ተገልጾልናል። የወያኔው ተላላኪ ሲሳይ ኪዳኔ የህጋዊው ሲኖዶስ አባል የሆኑትና በአገር ጉዳይ ላይ የግንባር ስጋ በመሆን እጅግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኙትንና የላስ ቬጋስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን በማጠናከርና አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ታላቅ ስራ የሰሩትን አቡነ መቃሪዎስን እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ አዋርዶና ህይወታቸው ላይ አደጋ በመደቀን ላስ ቬጋስ ከተማ እንዳይመለሱ በማድረግ አሳፋሪ ድርጊት ፈጽሞባቸዋል።በዚም ድርጊቱ ሎስ አንጀለስ ከሚገኘው የወያኔ ኢምባሲ ከፈተኛ ምስጋና እንደተቸረው ውስጥ አወቅ ወገኖች ይናገራሉ።

ከዚህም በተጨማሪ የላስ ቬጋስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በስደት በሚገኘው ሲኖዶስ ስር የሚተዳደር ሆኖ እያለ የሲኖዶሱን አባላት ጳጳሳት ፎቶግራፍ በሙሉ በቤተክርስቲያኑ ግርግዳ ላይ ተሰቅሎ ሲገኝ የአቡነ መቃሪዎስን ግን ከግርግዳ ላይ አውርዶ ሲሳይ ኪዳኔ ከጥቂት ባልደረቦቹ ጋር እንደጣለው ተጠቁመናል። ሲሳይ ኪዳኔ ከአሁን በፊትም የላስ ቬጋስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ከህጋዊው ሲኖዶስ ወጥቶ ገለልተኛ ይሁን እያለ ውስጥ ውስጡን ቅስቀሳ ሲያካሄድ እንደነበር ተገልጾልና። ሲሳይ ኪዳኔ ይህንን ሁሉ መሰሪ ድርጊት እየፈጸመ ምዕመናንን ለማወናበድ ጉልበቱንና ገንዘቡን ለቤተክርስቲያን እንደሚያጥፋ ለማስመሰል ተፍተፍ ሲል እንደሚታይና በዚህም ድርጊቱ ብዙ ምዕመናንን በማወናበድ ጠልፎ ለመጣልና ለሱ ደጋፊ ለማድረግ ችሏል ተብሏል። አብዛኛው ምዕመናን ቤተክርስቲያን የሚሄደው ከፈጣሪ ለመገናኘትና ከእለታዊ የኑሮ ውጣውረድና ፈተና እረፍት ለማግኘት ስለሆነ በረቀቀና በተደራጀ ሁኔታ እነሲሳይ ኪዳኔ የሚያካሂዱትን ተንኮል እግር በግር ለመከታተልና እርምጃ ለመውሰድ ጊዜም ሆነ ግንዛቤው የለውም።

ተሻገር ከልካይ ከወያኔ ኢምባሲ ጋር በመተባባር የውክልናና ሰነድ ማረጋገጥ ስራ በመስራት የሚተዳደር ግለሰብ ነው። ይህ ግለሰብ በስራው አጋጣሚ እጁ የገባውን የባለጉዳዮች የግል መረጃና ጉዳይ ስነ ምግባር በጎደለው ሁኔታ ከባለጉዳዮቹ ጋር ሲጣላ መረጃችሁን አጋልጣለሁ እያለ ሲያስፈራራ እንደነበር ሁኔታውን የሚያውቁ ሰዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል ተብሏል። ተሻገር ይህንን የመሰለ ወራዳ ድርጊት እየፈጸመ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ሲፈተፍትና ምዕመናንን ሲያወናብድ ሊያስቆመው የሚችል አካል አለመኖሩ ብዙዎች ምዕመናንን እንዳሳዘነ ታወቋል።

ተሻገር ከልካይ ከወኔው የውስጥ አርበኛ ሲሳይ ኪዳኔ ጋር በመመሳጠር በምዕመናን አንጡራ ሀብት የተገዛ ቤተክርስቲያን ለመንጠቅ ቀን ለሊት እየሸረበና እያውጠነጠነ ስለሚገኝ ምዕመናን በፍጥነት እርምጃ መውሰድ ይገባቸዋል የሚሉ ምዕመና ብዙዎች መሆናቸውም ተገልጾልናል።ይህም የተፈጠረው ጉዳይ ይህንን ሰሞንን በላስ ቬጋስ ከተማ ውስጥ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ትልቅ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል። ምዕመንናን ላይ ላዩን ሳይሆን ጠበቅ አድርገው የቤተክርስቲያናቸውን ጉዳይ በመከታታል በሶስት ፈረቃ እየሰሩ በበረሃ የደከሙበትን ቤተክርስቲያን በወያኔ ከመነጠቅ መከላከል እንደሚገባቸው ሊረዱ ይገባል ተብሏል። የላስ ቬጋስ ህዝብ በለንደን፣ አትላንታ፣ዋሽንግተን ዲሲ፣ ናሽቪል፣ ዳላስ፣ ሲያትል፣ ቶሮንቶና ሌሎችም ከተሞች በወያኔ ተላላኪዎች የደረሰው ጥቃት በነሱም እንዳይደርስ በሙሉ ኃላቸው ቤተክርስቲያናቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል።