ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አምስተርዳም ገባ፤ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል – ቪዲዮ

ከሀገር እንዳይወጣ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ጉዞውን ወደ ኔዘርላንድ ያቀናው አንጋፋው ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ በኔዘርላንድ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል ተደረጎለታል።

በስፍራው የተለያዩ የሚዲያ ባለሙያዎችና የእስክንድርን መምጣት በጉጉት ሲጠባበቁ የነበሩ በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአበባ ጉንጉን ያበረከቱለት ሲሆን የቄሮ ተወካዮችም የአባ ገዳ ስካርፍ አልብሰውታል።

እስክንድርም አጭር ንግግር ያቀረበ ሲሆን በንግግሩም ለኢትዮጵያ የሰላምና የዲሞክራሲ ትግል እንዲሁም በየእስር ቤቱ ላሉ ዜጎች በየጊዜው ተቃውሞ ሲያቀርቡ ለነበሩ የዲያስፖራ አባላት ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል።

“ጩሀታችሁና ትግላችሁ ከንቱ አልቀረም” በማለት አሁን በሀገሪቱ ውስጥ እየታዩ ያሉ የለውጥ ጭላንጭሎችን እንደ ማሳያ አቅርቧል።

VIDEOS