የሕዝብ ፍሬ ያፈራው የባህርዳሩ ጉባዬ ፤ ለኢሕአዴጉ ጠሚ ዶክተር አብይ ላይ ትልቅ ብድርና እዳ ያሸከመ የሕዝብ መድረክ ነበር (ምንሊክ ሳልሳዊ)

(ምንሊክ ሳልሳዊ) – የሕዝብ ፍሬ ያፈራው የባህርዳሩ ጉባዬ ፤ ለኢሕአዴጉ ጠሚ ዶክተር አብይ ላይ ትልቅ ብድርና እዳ ያሸከመ የሕዝብ መድረክ ነበር። የኢሕአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር በባህር ዳር ባደረገው ሕዝባዊ ኮንፈረንስ ላይ ሕወሓት እንዳሰበው ሳይሆን የሕዝብ ብሶት የተደመጠበት የወያኔ ገበና የተጋለጠበት ፍሬ ያፈራ ስብሰባ ነበር። ሕዝቡ መተንፈስ ያለበትን ሁሉ ተንፍሶ ወደ ተግባር እንዲገባ አስረግጦ ተናግሯል።ትላንትና ጠሚው ጎንደር ላይ የጎንደር ሕዝብ እያለ ባደረገው ንግ ግር የተቆጩት አቶ ገዱ በዛሬው የባህርዳር ስብሰባ የ አማራ ሕዝብ ብሎ እንዲናገር በጎ ምክራቸውን መለገሳቸውን የስብሰባው ምንጮች ይጠቁማሉ።

ባለፉት አመታት የላሸቀና ወኔው የሞተ ሱሰኛ ወጣትን ለማፍራት ሲተጋ የነበረው ሕወሓት የተኮላሸበት ወላጆች የነቁ ወጣቶች የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች እስኪበቃቸው የተናገሩበት ታላቅ ሕዝባዊ ስኬት ነበር። የክልሉ የተፈጥሮ ሃብት እየተበዘበዘ ለሌላ ክልል ማልሚያ መዋሉ ፣ የወልቃይት ጉዳይ ፣ ከኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ግብር ከፋይ አማራ ክልል ሆኖ አንድም ኢንዱስትሪና የላማት ማእከል ሲልም የወጣቶች መዝናኛ ያልተሰራለት መሆኑን ሕዝቡ በሰፊው ተናግሯል። ፖለቲካ በሃይማኖት ውስጥ ገብቶ እንደሚበጠብጥ የባለስልጣኖች እጅ ረዥም መሆኑ በፊትለፊትና በተዘዋዋሪ በመናገር ለዶክተር አብይ ላይ ትልቅ ብድርና እዳ ያሸከመ የሕዝብ መድረክ ነበር።

በቁጭትና በእልህ ትላልቅ ቁምነገሮች የተነሱበት የባህርዳሩ የሕዝብ መድረክ የኢሕአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያስደነገጠ ነበር። የዶክተር አቢይ ሁኔታ ለመገመት አስቸጋሪና ከባድ እየሆነ መጥቷል፤ የሕወሓት ሰዎች ያልተገኙበት ይህ መድረክ በግልጽነት የተካሔደ ሲሆን ሕወሃት ሲነዛው የነበረው ባህርዳር ላይ ካድሬ ብቻ ነው ስብሰባው ላይ የሚገባው ፕሮፓጋንዳ ከመክሸፉም በላይ የ አማራ መገናኛ ብዙሃን ጠንካራ ቃላቶች ሲነገሩ ስርጭቱን ያቆራርጥና ክላሲካል ማሰማቱ ት ዝብት ላይ ጥሎታል። ሕዝቡ ወሬ ይብቃ ወደ ተግባር ይገባ ብሏል። “ብአዴን አማራን አይወክልም!”,,,, “አማራ በራሱ ልጆች ይተዳደር!” #MinilikSalsawi