ብፁዕ አቡነ አብርሃም: ጠቅ/ሚኒስትሩ ስለኢትዮጵያዊነት በተናገሩት እንዲጸኑ አበረታቱ፤በቤተ ክርስቲያን ላይ ስለሚፈጸመው በደል አሳሰቡ-“ስምን ፈረሰኛ አይቀድመውምና ልጄ ተጠንቀቅ”

ተቀባይነትን ያስገኘላቸውና ተደናቂነትን ያተረፈላቸው፣ ከበዓለ ሢመታቸው ጀምሮ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ በማድረግ የሚገልጹባቸው ውብና ወርቃማ ቃላት በመኾናቸው፣ ስለ ተግባራዊነታቸው ዘወትር ሊያስቡበት ይገባል፤ ኢትዮጵያን የማያውቅ ትውልድ እየተፈጠረ በመኾኑ፣ በአስተዳደር ዘመናቸው፣ የአንዲት እናት ሀገር ልጆች፣ የጠላት መሣሪያዎች ኹነን፣ በጎጥና በድንበር ተከላለን ዐይንህ ላፈር የምንባባልበት