በደቡብ አፍሪካ የሚኖር የኢሕአዴግ ተቃዋሚ የሆነው ገዛኸኝ ገ/መ (ነብሮ) ከበርካታ የወያኔ ዛቻ በኃላ ተገደለ ።

አሳዛኝ ዜና


በደቡብ አፍሪካ የሚኖረው የኢትዮጲያ መንግስት ጠንካራ ተቃዋሚነቱ ታጋይነቱ የሚታወቀው ገዛሃኝ ገብረ መስቀል (ነብሮ) ትላንት ማምሻውን በግፍ መገደሉ ታውቋል።

በፓርኪንግ ቦታ ላይ ባለቤቱን እየጠበቀ ባለበት በተተኮሰበት ተደጋጋሚ ጥይት መሞቱን ለመረዳት ተችሏል። ነብሮ በሀገር ወዳድነቱ እና በጠንካራ ተቃዋሚነቱ በደቡብ አፍሪካ በሚገኙም ሆነ በሌላው አለም በሚገኙ ኢትዮጲያዊያን የሚታወቅ ነው። ሐምሳ አለቃ ገዛኸኝ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር አየር ወለድ ነበር ።


በግፍ በመገደሉ አዝነናል ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እንመኛለን ።