የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የብአዲንና የኦሕዴድ አመራሮች ጫና እየፈጠሩ ነው

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የብአዲንና የኦሕዴድ አመራሮች ጫና እየፈጠሩ ነው ። ሕወሓት አዋጁ ቢነሳም በመከላከያ ሰራዊቱ የሚመራው ኮማንድ ፖስት ስራውን መቀጠል አለባት በማለት እየተከራከረ ይገኛል ።

የክልል ባለስልጣናትና ሕዝቡ ከአከባቢያችን የአግአዚ ሰራዊት ይውጣልን በማለት እየጠየቁ ይገኛሉ ። ብአዲንና ኦሕዴድ ውስጥ ያሉ ሆድ አደሮች ከሕወሓት ጎን በመቆም  ኮማንድ ፖስቱ ስራውን ይቀጥል  በማለት እየተናገሩ ይገኛሉ ። ሰሞኑን የወጡ ሪፖርቶች እንደጠቆሙት ኮማንድ ፖስቱ ለጠቅላይ ምኒስትሩ ሪፖርት ለማቅረብ ፈቃደኛ አለመሆኑን አሳይቷል ። ቆንጂት ስጦታው ።