የሰብአዊ መብት ረገጣ የፈጸሙ ግለሰቦች ለፍርድ አልቀረቡም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2010) በኢትዮጵያ በአገዛዙ ታጣቂዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ረገጣዎችና ወንጀሎች ተጣርተው ፈጻሚዎቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዳልተደረገ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሪፖርት አመለከተ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2017 ሪፖርት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባሰፈረው የሰብአዊ መብት አያያዝ በሃገሪቱ ተጠያቂነት ባለመኖሩ በርካታ የሰብአዊ ጥሰቶች በመፈጸም