ትህነግ/ህወሓት በወልቃይት ላይ የፈፀማቸው 8 ዋና ዋና ወንጀሎች

ትህነግ/ህወሓት በወልቃይት ላይ የፈፀማቸው 8 ዋና ዋና ወንጀሎች

(ሰመጉ ወልቃይት ላይ ስለተፈፀመው በሪፖርቱ ያሰፈረው አጭር መግለጫ)

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ገና ትጥው ትግል ላይ ከነበረበት ከ1983 ዓም በፊት ጀምሮ የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔተኝነት ማንነት ጥያቄ ከማንሳቱ ጋር በተያያዘ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በዚህ መግለጫ በዝርዝር ቀርበዋል። በዚህ ሪፖርት ከተገለፁትና በአካባቢው ባለስልጣናት በሕዝቡ ላይ ከፈፀሙት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ ዋናዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው:_

1) ግድያ:_ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ያነሱ 34 የወልቃይት ተወላጆች ግድያ ተፈፅሞባቸዋል
2) ታፍኖ መውሰድ:_ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት ቁጥራቸው 93 የሆኑ ሰዎች በተለያዩ ጊዜያት ታፍነው ተወስደዋል። እስካሁን ድረስ ያሉበት አይታወቅም።

3)ድብደባና ማሰቃየት:_ የአካባቢው ባለስልጣናት የማንነት ጥያቄ ባነሱ ዜጎች ላይ ድብደባና ማሰቃየት ፈፅመዋል

4)ሕገ ወጥ እስራት:_ ከማንነት ጥያቄው ጋር በተያያዘ 17 ሰዎች ሕገወጥ እስራት ተገፅሞባቸዋል

5) የእርሻ መሬት፣ የመኖሪያ ቤትና ንብረት መነጠቅ:_የወልቃይት አርሶ አደሮች በተለያዩ ጊዜያት የእርሻ መሬታቸው፣ የእርሻ መኪኖቻቸው እንዲሁም በድካማቸው ያመረቱትን ምርት በሙሉና በከፊል በአካባቢው ባለስልጣናት ተነጥቀዋል።

6)መሳርያ መንጠቅ:_የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ደጋፊዎች ናችሁ በሚል ብቻ አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች መሳርያቸውን ተነጥቀዋል።

7) ከመኖርያ መፈናቀል:_የወልቃይት ሕዝብ አማራ ብሔርተኝነት ማንነት ጥያቄ በማንሳቱ ምክንያት የአካባቢው ባለስልጣናት የሚፈፅሙትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በመሸሽ ዜጎች ከመኖርያቸው ተፈናቅለው ለስደት ተዳርገዋል።

8) አድልዎና አስተዳደራዊ በደል:_ ከቋንቋ፣ ከባህል፣ ከኢኮኖሚ፣ ከፍትሕ አሰጣጥና ከአስተዳደር ጋር በተያያዘ አድልዎና በደል ተፈፅሞባቸወል።

(ይህ ሪፖርት ግንቦት 24/2008 ዓም የወጣ ሲሆን በአማራ ክልል ከነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሰበብ በወልቃይት ተወላጆች ላይ የተፈፀመውን የጅምላ እስር፣ ግድያ፣ ማሳደድና ሌሎች ጥሰቶች አላካተተም። ሪፖርቱ ለመንግስት ተቋማትም ደርሷል። ሰመጉ በኢትዮጵያ ብቸኛው ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ተቋም ነው። ሰብአዊ መብት ጉባኤ (ሰመጉ)፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽም ከሚባለውና በመንግስት ከሚመራው ተቋም የተለየ ተቋም ነው)