ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ችግር

ከስድስት ወራት በፊት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሼ ዞን በተከሰተ ግጭት የተፈናቀሉ ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች ዘላቂ መፍትሄና ድጋፍ ሳያገኙ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በሚገኝ መጠለያ ውስጥ ይገኛሉ።