ወቅታዊዉ ሁኔታ በምሥራቅና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከሰሞኑ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተቃዉሞ እንቅስቃሴ መኖሩ እየተነገረ ነው። የክልሉ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት ከሆነም የተቃውሞው መነሻ የአስተዳደር ብልሽት እና ሙስና ነው። ለዚህም የክልሉ ፕሬዝደንትን ተጠያቂ በማድረግ ከስልጣናቸው እንዲነሱ እንደሚጠይቁም እነዚሁ እማኞች ተናግረዋል።