የምዕራብ ጉጂ ዞን ግጭት ረግቧል

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን የኦሮሞ እና የጌዲኦ ተወላጆች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ቀስ በቀስ ወደ መኖርያ ቀያቸዉ እየተመለሱ እንደሆነ፤ ለጣብያችን መረጃዉን ያደረሱን የዓይን እማኞች ገለፁ። እንዲያም ሆኖ በግጭቱ የተፈናቀሉትና በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በተጠለሉበት ቦታ የሚያገኙት ርዳታ በቂ እንዳልሆነ